ደህንነቱ የተጠበቀ ኢሜይል እንዴት መጠቀም እንደሚቻል

ኢንክሪፕት የተደረገ መልእክት (ደህንነቱ የተጠበቀ መልእክት በመባልም ይታወቃል) ከእርስዎ ሌላ ማንም ሰው የምንልክልዎትን መረጃ እንዳያነብ ይከለክላል። ይህንን ለእርስዎ ገመና እና የማንነት ስርቆትን ለመከላከል እንጠቀምበታለን።

OED የተላኩ ደህንነታቸው የተጠበቀ መልዕክቶችን መክፈት

የኦሬገን የሥራ ስምሪት መምሪያ ለሥራ አጥነት ኢንሹራንስ ጥቅማጥቅሞች ለሚያስገቡ ሰዎች የምንልክላቸውን ደህንነታቸው የተጠበቀ መልዕክቶችን ለማግኘት የማይክሮሶፍት ኦፊስ መልእክት ምስጠራን (Encryption) ይጠቀማል።

ለእርስዎ የምናስተላልፈው መልእክት ደህንነት በጣም አስፈላጊ ነው። የእርስዎን መረጃ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ሚስጥራዊ ለማድረግ ጠንክረን እንሞክራለን። የማንነት ስርቆት የመሳሰሉትንም ማጭበርበር መከላከል እንፈልጋለን

የማይክሮሶፍት ኦፊስ መልእክት ምስጠራ ደህንነትን ይሰጣል እና ለመጠቀም ቀላል ነው።

ኢንክሪፕትድ የተደረገ መልእክት ከኛ ከተቀበሉ በኢሜል ውስጥ ያለውን "ደህንነቱ የተጠበቀ መልእክት አንብብ" ወይም “Read Secure Message” የሚለውን አገናኝ ጠቅ ያድርጉ። ይህ ከአስተማማኝ የመልእክት ማእካል (ፖርታል) ጋር ያገናኘዎታል።

ከዚያ፣ የሚከተሉትን ያደርጋሉ፤

  • በኢሜል አድራሻዎ የማይክሮሶፍት መለያ (አካወንት) ይፍጠሩ፤ ወይም
  • ወደ ኢሜልዎ በተላከ የአንድ ጊዜ የይለፍ ኮድ ይግቡ።

የአንድ ጊዜ የይለፍ ኮድ ከረሱ ኢሜልዎን ይክፈቱ እና አዲስ የይለፍ ኮድ ለመቀበል አገናኙን እንደገና ጠቅ ያድርጉ። እያንዳንዱ የይለፍ ኮድ ከተላከ በኋላ ለ15 ደቂቃዎች ነው የሚሰራው።

በማይክሮሶፍት ኦፊስ መልእክት ምስጠራ ደህንነታቸው የተጠበቁ መልዕክቶችን ስለመክፈት የበለጠ ይረዱ

የቆዩ መልዕክቶችን መድረስ

በነሐሴ 2022 የማይክሮሶፍት ኦፊስ መልእክት ምስጠራን መጠቀም ከመጀመራችን በፊት የላክንልዎ የተመሰጠሩ መልእክቶች አይገኙም። በቀደመው ደህንነቱ የተጠበቀ የመልእክት መላላኪያ ስርዓት የላክንልዎ የአስተዳደር ውሳኔ ቅጂ ከፈለጉ እባክዎን ለእርዳታ ያግኙን፡፡