የራስ-ቀጣሪ እርዳታ

ወደ ንግድ ስራ መለወጥ የሚችል ሙያዊ ችሎታ ወይም ፍላጎት አለዎት? የስራ አጥነት መድን ጥቅማ ጥቅሞችን እያገኙ በሚቀጥሉበት ጊዜ ይህ እንዲሆን ለማድረግ የራስ-ቀጣሪ እርዳታ (SEA, በእንግሊዝኛ ምህፃረ ቃል ነው) ፕሮግራም የእርስዎ እድል ሊሆን ይችላል።

በየሳምንቱ በሚካሄዱ ዌብናርዎቻችን የበለጠ ይረዱ

ስለ መመዘኛዎች እና ለፕሮግራሙ ማመልከት በተመለከተ ጥያቄዎች አሉዎት? በየሳምንቱ በኦንላይን ዌቢናር ላይ የበለጠ መማር እና ጥያቄዎችን መጠየቅ ይችላሉ፣ ለግል ስራ እርዳታ መርሃ ግብር መግቢያ፡ ( Introduction to the Self-Employment Assistance Program )። በየሳምንቱ አርብ ከጧቱ በአካባቢው የሰዓት አቆጣጠር በ9፡00 ሰዓት ላይ በዙም ለመቀላቀል ኮምፒውተርዎን ወይም ስልክዎን ይጠቀሙ።

ማስታወሻ፡ ዌቢናሮች በሚከበሩ የመንግስት በዓላት ላይ ይሰረዛሉ።

ዌብናሮች በእንግሊዝኛ ብቻ ናቸው ፣ አስተርጓሚነትን ለመጠየቅ ዕርዳታ ይፈልጋሉ?

በአካባቢው የሰዓት አቆጣጠር ከጧቱ በ9፡00 ሰዓት ይቀላቀሉን።
Nine rowers propel a narrow boat along the Willamette River under the Ross Island Bridge in Portland.

የራስ-ቀጣሪ እርዳታ (SEA) ፕሮግራም ምንድን ነው?

የSEA ፕሮግራም የስራ አጥነት መድን ጥቅማጥቅሞችን ለሚቀበሉ — እና ጥቅማጥቅሞቹ ሊያልቅባቸው ለሚችሉ — እና የራሳቸውን ንግድ ለመጀመር ፍላጎት ላላቸው ሰዎች የሚሆን ነው።

በSEA ፕሮግራም አማካኝነት ጥቅማጥቅሞችን ለማግኘት በተለምዶ የሚፈለጉት የስራ ፍለጋ መስፈርቶች ከሌሉ እስከ 26 ሳምንታት የሚደርስ የስራ አጥነት ጥቅማጥቅሞችን ማግኘት ይችላሉ፤ በዚህም ሙሉ ጊዜዎን በራስ-ቅጥር ስራዎ ላይ ማተኮር እና ንግድዎን መገንባት ይችላሉ። እንዲሁም ደግሞ ከአዲሱ ንግድዎ የሚያገኙትን ገቢ ያስቀምጣሉ።

ከ1,500 በላይ የኦሪገን ዜጎች የራሳቸውን ንግድ በተሳካ ሁኔታ እንዲጀምሩ አግዘናቸዋል።

ለSEA ፕሮግራም እንዴት ማመልከት እችላለሁ?

በቅደሚያ፣ ብቁ መሆንዎን ለማወቅ ለUI ልዩ ፕሮጋራሞች ማዕከል በ 503-947-1800 ወይም 800-436-6191 ይደውሉ።

በመቀጠልም፣ የእርስዎን የSEA መተግበሪያ እና የንግድ ስራ አዋጭነት ሉህንያነጋግሩን ፖርታል/Contact Us portal በኩል ይላኩልን። ይህ ቅጽ በእርስዎ ቋንቋ አይገኝም። እባክዎ ለማስተርጎም ወይም ለትርጉም ያነጋግሩን። አገልግሎቶቻችንን መጠቀም እንዲችሉ OED ነፃ እገዛን ይሰጣል። ይህንን እንዴት ማድረግ እንደሚቻል በፍላጎት እርዳታ? ገጽ ላይ መረጃ አለ።

እንዲሁም የተጠናቀቀውን የስራ ሉህ ወደ Oregon Employment Department, PO Box 14518, Salem, OR 97309 መላክ ይችላሉ። ​የስራ ሉህ የንግድ ገበያውን ለመረዳት ያግዝዎታል። ለንግድዎ ስኬታማነት በቂ የደንበኛ ፍላጎት እንዳለ ለማወቅ ሊያግዝ ይችላል።

ማመልከቻዎን እንገመግመዋለን እና የብቁነት መስፈርቶችን ያሟሉ እንደሆነ እናሳውቀዎታለን። በቀጣይ ምን ማድረግ እንዳለብን አቅጣጫዎችን እናስቀምጣለን።

የፕሮግራሙ መስፈርቶች ምንድን ናቸው?

የንግድ አዋጭነት ሉህ ማጠናቀቅ እና የንግድ እቅድ መፍጠር አለብዎት። አንዴ ከተፈቀደ በኋላ፣ ጥቅማጥቅሞችን ለሚጠይቁበት ለእያንዳንዱ ሳምንት የSEA ሳምንታዊ የይገባኛል ጥያቄ ቅጽን በመጠቀም የራስ-ቅጥር ስራዎችን መመዝገብ አለብዎት። ወደ ውስጥ ለመላክ በቅጹ ላይ ያሉትን መመሪያዎች ይከተሏቸው።

መመሪያ የት ማግኘት እችላለሁ?

የኦሪገን የአነስተኛ ንግድ ልማት ማዕከል አውታረመረብ (SBDC, በእንግሊዝኛ ምህፃረ ቃል ነው) የንግድ ስራ ጅምር ማማከር እና ምክር ሊሰጥ ይችላል። ባለሙያዎች የንግድ እቅድና የአዋጭነት ጥናትን አንድ ላይ እንዲያዘጋጁ ይረዱዎታል።

ስላሉት መመሪያዎች እና አገልግሎቶች የበለጠ ለማወቅ፣ የአነስተኛ ንግድ ልማት ማከል አውታረመረብን በ
541-463-5250 ወይም support@oregonsbdc.org ያነጋግሩ።

የSEA ፕሮግራም ንግዴን ለመጀመር ወይም ለማስፋፋት የሚረዳኝ እንዴት ነው?

የSEA ፕሮግራም የስራ አጥነት መድን ጥቅማጥቅሞችን በመቀበል ጊዜ ስራ ለመፈለግ የሚያስፈልገውን መስፈርት ያስወግዳል። ይህ የራስዎን ንግድ ለመጀመርና በሱ ገቢ ለማግኘት እንዲጀምሩ የበለጠ ጊዜ ይሰጥዎታል። ከንግድዎ ትርፍ ማግኘት እንደጀመሩ፣ ሙሉውን ሳምንታዊ የጥቅማጥቅም ክፍያ እየተቀበሉ ያንን ገቢ ያቆያሉ።

ወደ የSEA ፕሮግራም ከመቀበሌ በፊት የንግድ ስራ እቅዴን ማጠናቀቅ የግድ አለብኝ?

የለብዎትም፣ የእርስዎን SEA ፕሮግራም ማመልከቻ እና የንግድ አዋጭነት ሉህ በሚያመለክቱበት ጊዜ ብቻ እንፈልጋለን። የንግድ እቅድዎ ጊዜው የሚደርሰው ማመልከቻዎን ከተቀበልን ከ45 ቀናት በኋላ ነው።

ምን አይነት ንግዶች የተከለከሉ ናቸው?

በኦሪገን ውስጥ ህጋዊ ለሆኑ፣ ለመንግስት ስፖንሰር ተስማሚ የሆኑና በአካባቢያቸው ለሚስማሙ ንግዶች ማመልከቻዎችን እናጸድቃለን። በአዋሳኝ ስቴቶች ህጋዊ የሆኑ አንዳንድ ንግዶች በኦሪገን ህጋዊ አይደሉም። በSEA ፕሮግራም ውስጥ ያልተፈቀዱ የንግድ ሥራዎች ምሳሌዎች የማሪዋና ማከፋፈያ፣ ማሪዋና ወይም ካናቢስ አብቃይ እና “እፅ አቀባይ” ስራን ያካትታሉ።

ለSEA ፕሮግራም ከተፈቀደልኝ በኋላ ምን ማድረግ አለብኝ?

ወደ SEA ፕሮግራም በመቀበል በ45 ቀናት ውስጥ፣ የንግድ መለያ ቁጥርዎን፣ የፌደራል አሰሪ መለያ ቁጥርዎን እና የንግድ እቅድዎን ማቅረብ አለብዎት። የፕሮግራሙ ማፅደቂያ ማሳወቂያ የሚያስፈልጉትን ዝርዝሮች፣ ቅጾች እና አገናኞች ያካትታል።

በተጨማሪም፣ ለስራ አጥ መድን ጥቅማጥቅሞች መደበኛ ሳምንታዊ የይገባኛል ጥያቄዎችን ከማቅረብ ይልቅ፣ የSEA ሳምንታዊ የይገባኛል ጥያቄ ማረጋገጫዎችን መላክ ያስፈልግዎታል። ለመላክ በቅጹ ላይ ያሉትን መመሪያዎች ይከተሉ። ቅጾች በፖስታ አሊያም በፋክስ ሊላኩ ይችላሉ፦

ደብዳቤ

Oregon Employment Department

PO Box 14518

Salem, OR 97309

ፋክስ

503-947-1833

ጥያቄዎች አሉዎት?

ጥያቄዎች ካሉዎት፣ በያነጋግሩን ቅጽ በኩል መልእክት ይላኩ።

የእኔ የSEA ጥቅማጥቅሞች ለምን ያህል ጊዜ ይቆያሉ?

ያለዎት መደበኛ የስራ አጥነት መድን የይገባኛል ጥያቄ የ SEA ጥቅማ ጥቅሞችን ይወስናል። ከፍተኛ የጥቅማጥቅም መጠን ላይ ሲደርሱ የ SEA የይገባኛል ጥያቄዎ ጊዜው ያልፍበታል።

የእኔ ጥቅማጥቅሞች ቀሪ ሂሳብ ምን እንደሆነ ለማየት እንዴት መፈተሸ እችላለሁ?

ቀሪ ሂሳብዎን ለመፈተሽ የUI ልዩ ፕሮግራሞች ማዕከልን በ 503-947-1800 ወይም 800-436-6191 ይደውሉ።