ጊዜው ያለፈባቸው የይገባኛል ጥያቄዎች እና የይገባኛል ጥያቄን እንደገና በማስጀመር ላይ
ከስራ አጥነት መድን ፕሮግራም ጥቅማጥቅሞችን ለማግኘት ሳምንታዊ የይገባኛል ጥያቄ ካላቀረቡ የይገባኛል ጥያቄዎን እንደገና ማስጀመር ይኖርብዎታል። ወደ ሥራ ከተመለሱ በኋላ እንደገና ከሥራ ከተባረሩ ይህ የተለመደ ነው። አስቀድመው መጠባበቂያ ሳምንት ላይ ካገለገሉ የይገባኛል ጥያቄዎን እንደገና ሲጀምሩ ሌላ መጠባበቂያ ሳምንት ማገልገል የለብዎትም።
ለጥቅማጥቅሞች ካመለከቱበት ጊዜ ጀምሮ ከአንድ ዓመት በላይ ከሆነ፣ የይገባኛል ጥያቄዎ ጊዜው ሊያልፍበት ይችላል።
የይገባኛል ጥያቄዬን እንደገና ማስጀመር ያለብኝ ለምንድን ነው?
የሚከተለው ከሆነ ጥያቄዎን እንደገና ማስጀመር ይኖርብዎታል፦
- ሳምንታዊ የይገባኛል ጥያቄ አላስገቡም።
- እርስዎ በህመም፣ በዕረፍት ወይም በሌላ ምክንያት ሳምንታዊ የይገባኛል ጥያቄ ማስገባት አቁመዋል።
- ሳምንታዊውን የይገባኛል ጥያቄ ማስገባት ረስተዋል።
- ለአንድ ሳምንት ወይም ከዚያ በላይ ሙሉ ሰዓት ሠርተዋል።
- በሳምንት ውስጥ ከእርስዎሳምንታዊ የጥቅማጥቅም መጠን በላይ አግኝተዋል።
የይገባኛል ጥያቄዎን እንደገና እስከሚጀምሩ ድረስ ሳምንታዊ የይገባኛል ጥያቄዎችን ማስገባት አይችሉም።
የይገባኛል ጥያቄዬን እንዴት እንደገና ማስጀመር እችላለሁ?
Frances Online፦ በማንኛውም ጊዜ Frances Online ውስጥ የይገባኛል ጥያቄዎን እንደገና ማስጀመር ይችላሉ። ተጨማሪ እገዛ ለማግኘት ይህን የደረጃ በደረጃ መመሪያ ይከተሉ።
በስልክ፦ በUI ማእከል ውስጥ ካለ ወኪል እርዳታ ለማግኘት 877-345-3484 ላይ ይደውሉ።
የሚያስፈልገኝ መረጃ ምንድን ነው?
በቅርብ ጊዜ ሠርተው እንደነበረ ወይም በግል ሥራ ላይ የተሰማሩ መሆንዎን እንጠይቅዎታለን።
ይሠሩ ከነበረ፣ አንድ የይገባኛል ጥያቄ እንደገና ለመጀመር ሁሉም የቅርብ ጊዜ አሰሪዎች መረጃ ያስፈልግዎታል። ይህ የሚከተሉትን ያጠቃልላል፦
- የሰሩባቸውን ቀናት።
- የአሠሪዎ ስም፣ ስልክ ቁጥር እና አድራሻ።
- ከዚህ አሰሪ የሚያገኙት ደመወዝ እና ገቢ።
- ሥራ ላይ ያልተሰማሩበት ወይም የሙሉ ጊዜ ሥራ ያልሰሩበት ምክንያት።
በሌሎች ምክንያቶች የይገባኛል ጥያቄዎን ካቆሙ፣ የይገባኛል ጥያቄዎን ያቆሙበትን ምክንያት ማቅረብ ይጠበቅብዎታል።
የይገባኛል ጥያቄዬን እንደገና ከጀመርኩ በኋላ ምን ማድረግ ይኖርብኛል?
በየሳምንቱ፣ ለጥቅማጥቅሞች ብቁ ለመሆን የተወሰኑ ተግባራትን ማጠናቀቅ አለብዎት፦
- አብዛኛዎቹ የይገባኛል ጥያቄ አቅራቢዎች ለጥቅማጥቅሞች ብቁ ለመሆን ሥራ መፈለግ አለባቸው።
- ብቁ መሆንዎን ለማሳየት ሳምንታዊ የይገባኛል ጥያቄ ማቅረብ አለብዎት።
- በሳምንታዊ የይገባኛል ጥያቄዎች ገጽ ላይ ተጨማሪ ይወቁ።
ስለ ማመልከቻዎ፣ ስለ ሥራ ታሪክዎ ወይም ስለ ሌሎች ጥቅማጥቅሞች ብቁ መሆንዎን ለመወሰን ስለሚያስፈልጉ መረጃዎች የሚቀርቡ መጠይቆችን ይመልሱ። Frances Online ን እና ኢሜይልዎን በመደበኛነት ይፈትሹ እና ለማንኛቸውም መልዕክቶች ወዲያውኑ ምላሽ ይስጡ። የሁኔታ መልዕክቶች ገጽ ላይ ተጨማሪ ይወቁ።
የይገባኛል ጥያቄዬ ጊዜው ቢያልፍበትስ?
ከሥራ አጥነት መድን መርሃግብር የሚሰጡ ጥቅማጥቅሞች ላይ ትክክለኛ የሆኑ የይገባኛል ጥያቄዎች ጊዜያቸው ከማለፉ በፊት ለአንድ ዓመት ይቆያሉ። የይገባኛል ጥያቄዎ ጊዜው ካለፈበት፣ ለጥቅማጥቅም ብቁ መሆንዎን ለማወቅ እንደገና ማመልከት አለብዎት።
ለጥቅማጥቅሞች እንዴት ማመልከት እንደሚቻል በእንዴት ማስገባት እችላለሁ? ገጽ ላይ ይወቁ።