የስራ አጥነት መድን ምንድን ነው?
የስራ አጥነት መድን በራሳቸው ባልሆነ ጥፋት ስራ ላጡ ወይም ሰዓታቸው ለተቀነሰ ሰዎች ገንዘብ ይሰጣል። የስራ አጥነት መድን ጥቅማጥቅሞች ሳምንታዊ ክፍያዎች ሰዎች በንቃት ስራ ሲፈልጉ ይደግፋሉ።
ስራዎን ካጡ ወይም አሰሪዎ ሰዓትዎን ከቆረጠ፣ ለስራ አጥነት መድን ጥቅማጥቅሞች ማመልከት አለብዎት። ለሳምንታዊ ክፍያዎች ብቁ መሆንዎን ለማወቅ ወኪሎቻችን ያግዛሉ።
የጥቅማጥቅሞችን ካልኩሌተርን
ምን ያህል ለመቀበል ብቁ ሊሆኑ እንደሚችሉ ለማወቅ፣ ይህም የእርስዎ “የመነሻ ዓመት” ተብሎ በሚጠራው ጊዜ ውስጥ ባገኙት ገቢ ላይ ተመስርተው የጥቅማጥቅሞችን ካልኩሌተርን ይጎብኙ።
የጥቅማጥቅሞችን ካልኩሌተርንኦሪገን ውስጥ ለስራ አጥነት ዋስትና ብቁ የሆነው ማነው?
በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ከሚገኙ አምስት ሰዎች ውስጥ አራቱ በስራ ዘመናቸው ውስጥ በሆነ ወቅት የስራ አጥነት ክፍያ ያስፈልጋቸዋል። የሙሉ ጊዜ፣ የትርፍ ሰዓት እና ጊዜያዊ ስራዎችን ያጡ ሰዎች ለጥቅማጥቅም ክፍያ ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ።
በዩኤስ ውስጥ ለመስራት ፈቃድ ያለው ማንኛውም ግለሰብ ለስራ አጥነት ጥቅማጥቅሞች ብቁ ሊሆን ይችላል። ይህ የህዝብ እርዳታ ወይም የህዝብ ክፍያ አይነት አይደለም።
ብዙ ሰራተኞች ቀጣሪያቸው እንደ ጊዜያው ሰራተኞች ቢቆጥራቸውም እንኳ ለስራ አጥነት መድን ብቁ ይሆናሉ። ለጥቅማጥቅሞች ብቁ ስለመሆን የበለጠ ለማወቅ፣ ብቁ ነኝ? የሚለውን ይጎብኙበ
ለስራ አጥነት መድን የሚከፍለው ማነው?
የስራ አጥነት መድን በፍላጎት ላይ የተመሰረተ የህዝብ እርዳታ ወይም ደህንነት አይደለም። ለእነዚህ ጥቅማጥቅሞች የሚሆነው ገንዘብ ከኦሪገን አሰሪዎች የሚመጣ ሲሆን እነሱም ለስራ አጥነት መድን ትረስት ፈንድ መዋጮ ማድረግ አለባቸው። ገንዘቡ ከሰራተኞች ደመወዝ አይመጣም።
በዩኤስ ግምጃ ቤት የሚገኘው የኦሪገን የስራ አጥነት መድን ትረስት ፈንድ ለስራ አጥነት መድን ጥቅማጥቅሞችን ለመክፈል ብቻ ጥቅም ላይ ይውላል። በኦሪገን ራስ-ሚዛናዊ በሆነ የግብር ስርዓት የተነሳ ገንዘቡ በሀገሪቱ ውስጥ በጣም ጤናማ ከሆኑት አንዱ ነው።
ምን ማድረግ አለብኝ?
ጥቅማጥቅሞችን ለመቀበል ብቁ መሆንዎን ለማወቅ ለማመልከት፣ ለስራ አጥነት መድን የመጀመሪያ ጥያቄ ማቅረብ አለብዎት። በየሳምንቱ ሳምንታዊ የይገባኛል ጥያቄ ማቅረብም አለብዎት — የመጀመሪያ የይገባኛል ጥያቄዎን በሚያስገቡበት ሳምንት እንኳን ቢሆን። ስራ መፈለግ፣ መስራት መቻል እና ለስራ ዝግጁ መሆን ያስፈልግዎታል። አዲስ ስራ እገዛ ለማግኘት በWorkSource Oregon በኩል ይገኛል። ለስራ አጥነት መድን ጥቅማጥቅሞች እንዴት ማመልከት እንደሚችሉ የበለጠ መረጃን ማግኘት ይችላሉ።
ለኦሪጎናውያን የስራ አጥነት መድን ጥቅማጥቅሞችን በመስጠት ረገድ የቅጥር መምሪያው ሚና ምንድን ነው?
የቅጥር መምሪያ በፌደራል እና በክልል ህግ የተቋቋሙ መመሪያዎችን በመከተል በኦሪገን ውስጥ የስራ አጥነት መድን ፕሮግራምን ያስተዳድራል። ለፕሮግራሙ የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርገውን የአሰሪውን መዋጮች እንሰበስባለን፣ ማን ጥቅማጥቅሞች ለማግኘት ብቁ እንደሆነ እንወስናለን፣ ማጭበርበርን እንከላከላለን እና እንለያለን፣ እና ብቁ ለሆኑ ሰራተኞች ጥቅማጥቅሞችን እንከፍላለን።
ከመደበኛው የስራ አጥነት መድን ፕሮግራም በተጨማሪም፣ የቅጥር መምሪያው ለስራ አጥ ሰራተኞች ጥቂት ልዩ ፕሮግራሞችን ያከናውናል፣ ለምሳሌ ያህል፦ በግል ሥራ ለመሰማራት ለሚፈልጉ ሰዎች የሚሰጥ ራስን በራስ የመቅጠር ፕሮግራም እና ወደ ሥራ ለመመለስ አዲስ ክህሎቶች እያገኙ ላሉ ለተፈናቀሉ ሰራተኞች የስልጠና የስራ አጥ መድን ፕሮግራም። የበለጠ ለማወቅ፣ ተጨማሪ ፕሮግራሞችን ይጎብኙ።
የስራ አጥነት መድን እንዴት ኦሪገንን ይረዳል?
የስራ አጥነት መድን ለኦሪጋውያን እንዲሁም ማህበረሰባቸው ኢኮኖሚያዊ መረጋጋትን ይደግፋል። ሳምንታዊ ክፍያዎች ስራቸውን ያጡ ቤተሰቦችን እና ሰራተኞችን ይደግፋሉ።
ገንዘቡ ሰራተኞች ከስራ በተቀነሱባቸው ማህበረሰቦች ውስጥ የግዢ አቅምን ለመጠበቅ ይረዳል። ይህም እቃዎችን እና አገልግሎቶችን የሚያቀርቡ ሰራተኞችን ከሁለተኛ ደረጃ ስራ አጥነት ለመከላከል ይረዳል።
ክፍያዎቹ ኢኮኖሚያዊ አለመረጋጋቶችን በማለዘብ በማህበረሰቡ ውስጥ የሰለጠነ የሰው ሃይል እንዲኖር ያግዛሉ። የስራ አጥነት መድን መርሃ ግብር ሁሉን-አቀፍ ምጣኔ ሀብታዊ ድቀትን ለመከላከል ከሚረዱ ብዙ መሳሪያዎች ውስጥ አንዱ ነው።