የወረርሽኝ ፕሮግራሞች
የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለኦሪጋውያን ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ የፋይናንስ ችግር እና የስራ ማጣት ወቅት ነበር፣ እና የስራ አጥነት መድን ጥቅማጥቅሞች እንደሌሎች የኢኮኖሚ ድቀት ለኦሪጋውያን መረጋጋትን በመስጠት ረገድ ቁልፍ ሚና ተጫውተዋል። የቅጥር መምሪያ በወረርሹኙ ወቅት በርካታ አዳዲስ የፌዴራል መርሃግብሮችን እና የዘመኑን የስቴት መስፈርቶችን ተግባራዊ አድርጓል ቨ የበርካታ የፌዴራል እና የክልል ህግ አውጪ እርምጃዎች ውጤት — እና ከ 2019 ጋር ሲነፃፀር 600% የሚከፈልባቸው የይገባኛል ጥያቄዎች እና 1,400% የጥቅማጥቅሞችን በ 2020 ጨምሯል። ይህም ከ580,000 በላይ ጥቅማጥቅሞችን ከሚያገኙ ሰዎች እና በአንድ ዓመት ውስጥ (2020) ከተከፈለ ወደ $7.5 ቢሊዮን የሚጠጋ የUI ጥቅማጥቅሞች ጋር እኩል ነው።
በዚህ ገፅ ላይ የተዘረዘሩት መርሃ ግብሮች እና ግብዓቶች ከአሁን በኋላ ንቁ አይደሉም ወይም አዲስ የይገባኛል ጥያቄዎችን አይቀበሉም፣ ሆኖም አንዳንድ መረጃዎች በወረርሽኙ ወቅት ከመርሃ ግብሮቹ ተጠቃሚ ለሆኑ ሰዎች ጠቃሚ ሊሆኑ ይችላሉ።
በዚህ ገጽ ላይ:
- የአሜሪካ የማዳኛ እቅድ/American Rescue Plan (ARP)
- ቀጣይነት ያለው የእርዳታ ህግ (CAA)
- የኮሮናቫይረስ እርዳታ፣ እፎይታ እና የኢኮኖሚ ደህንነት (CARES) ህግ
- የፌዴራል የወረርሽኝ የስራ አጥነት ካሳ (FPUC)
- ሃውስ ቢል 3389
- የጠፋ የደመወዝ እርዳታ (LWA)
- ድብልቅ የስራ አጥነት ካሳ (MEUC)
- የወረርሽኝ የድንገተኛ ጊዜ የስራ አጥነት ካሳ (PEUC)
- የክፍያ ቼክ ጥበቃ ፕሮግራም (PPP)
- የወረርሽኝ የስራ አጥነት እርዳታ (PUA)
- እንደ ስራ አጥ የሚያስቆጥሩ ልዩ ሁኔታዎች
- የስራ አጥነት መጠበቂያ ሳምንት ማቋረጫ

የአሜሪካ የማዳኛ እቅድ/American Rescue Plan (ARP)
ARP ከማርች 14፣ 2021 እስከ ሴፕቴምበር 4፣ 2021 ድረስ የተወሰኑ ቀጣይነት ያላቸው የእርዳታ ህግ ጥቅማጥቅሞችን ያራዘመ የፌደራል የጥቅም ጥቅል ነበር። ARP የወረርሽኙን የድንገተኛ ጊዜ የስራ አጥነት ካሳ፣ የወረርሽኝ ስራ አጥነት እርዳታን እና የፌዴራል ወረርሽኝ ስራ አጥነት ካሳ ፕሮግራሞችን እስከ ሴፕቴምበር 4፣ 2021 ድረስ አራዝሟል።
ቀጣይነት ያለው የእርዳታ ህግ (CAA)
CAA በዲሴምበር 2020 የወጣው የፌዴራል ጥቅማጥቅሞች ጥቅል እስከ 11 ተጨማሪ ሳምንታት የሚዘልቅ የወረርሽኝ ስራ አጥነት እርዳታ ጥቅማጥቅሞችን የሚሰጥ፣ እስከ 11 ተጨማሪ የፌደራል የወረርሽኝ የስራ አጥነት ካሳ የሚሰጥ እና በኮቪድ-ነክ የፌዴራል ጥቅማ ጥቅሞች ላይ ተጨማሪ ለውጦችን የሚያስፈልገው ነው። እንዲሁም CAA ለድብልቅ ገቢ አግኚዎች ወይም ሁለቱንም የW-2 ደሞዝ እና የግል ስራ ገቢ ለሚያገኙ ሰዎች የድብልቅ የስራ አጥነት ካሳ ጥቅማጥቅሞች ፕሮግራምን አስተዋውቋል።
የኮሮናቫይረስ እርዳታ፣ እፎይታ እና የኢኮኖሚ ደህንነት (CARES) ህግ
የCARES ህግ በማርች 27፣ 2020 የተፈረመ የፌደራል የጥቅም ጥቅል ነበር። ከመቼውም ጊዜ በበለጠ በርካታ ሰዎችን በተለይም በኮቪድ-19 የተጎዱ ሰዎችን የስራ አጥነት ጥቅማጥቅሞችን እንዲያገኙ አስችሏል። ይህ ህግ የወረርሽኝ የስራ አጥነት እርዳታን፣ የፌደራል የወረርሽኝ የስራ አጥነት ካሳ እና የወረርሽኝ የአደጋ ጊዜ ስራ አጥነት ካሳ ፈጠረ።
የፌደራል ፕሮግራም የትርፍ ክፍያ እንዳይከፈል ማድረጊያ፦ የዩኤስ የሰራተኛ መምሪያ ብቁ ለሆኑ ጠያቂዎች የፌደራል ጥቅማ ጥቅሞችን ከመጠን በላይ ክፍያ የእንዳይከፈል ማድረጊያ አማራጭ ይሰጣል። ባለስልጣናቱ እርስዎ ለተጨማሪ ክፍያው ጥፋተኛ እንዳልሆኑ እና መልሰው መክፈልዎ የገንዘብ ችግርን እንደሚያስከትልብዎ ካወቁ እንዳይከፈል እንዲደረግልዎት ሊጠይቁ ይችላሉ። ይህ እንዳይከፈል ማድረጊያ በወረርሽኙ የአደጋ ጊዜ የስራ አጥነት ማካካሻ፣ የፌደራል ወረርሽኙ የስራ አጥነት ክፍያ፣ የወረርሽኝ የስራ አጥነት እርዳታ፣ የጠፋ የደመወዝ እርዳታ እና የተቀላቀሉ ገቢ ፈላጊዎች የስራ አጥ ካሳ ይመለከታል። የፌደራል እንዳይከፈል ማድረጊያን በኦንላይን መጠየቅ ይችላሉ። ይህንን እንዳይከፈል ማድረጊያ ለማጠናቀቅ እገዛ ከፈለጉ፣ በ503-947-1995 ይደውሉ። የአስተርጓሚ እና የትርጉም እገዛን መጠየቅ ይችላሉ።
የፌዴራል የወረርሽኝ የስራ አጥነት ካሳ (FPUC)
ማንኛውም አይነት የስራ አጥነት ጥቅማጥቅሞችን የሚያገኙ ሰዎች በሙሉ ከማርች 29፣ 2020 እስከ ጁላይ 25፣ 2020 ድረስ በየሳምንቱ ተጨማሪ $600 በ CARES ህግ መሰረት ያገኛሉ። ቀጣይነት ያለው የእርዳታ ህግ እና የአሜሪካ የማዳኛ እቅድ ከዲሴምበር 27፣ 2020 ጀምሮ እስከ ሴፕቴምበር 4፣ 2021 ድረስ የ FPUC ጥቅማጥቅሞችን በሳምንት በ$300 ቀጥሏል።
ሃውስ ቢል 3389
በጁላይ 27፣ 2021፣ ሀገረ ገዢዋ ኬት ብራውን በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ተፅዕኖ ለደረሰባቸው ቀጣሪዎች የስራ አጥነት መድን የደመወዝ ቀረጥ እፎይታ የሚሰጠውን ሃውስ ቢል 3389 ፈርማለች። ዕቅዱ ብቁ ቀጣሪዎች የ2021 የስራ አጥነት መድን ግብር ተጠያቂነታቸውን አንድ ሶስተኛውን እስከ ጁን 30 ቀን 2022 እንዲያዘገዩ እና ወለድና ቅጣቶችን እንዲያስወግዱ ፈቅዷል። ይህ እቅድ አንዳንድ የደመወዝ ግብሮችን በይቅርታም አልፏል። በተጨማሪም፣ ከ2022 እስከ 2024 ያለው የአሰሪው የስራ አጥነት መድን የግብር ልምድ ደረጃ ወደ ቅድመ ወረርሽኙ ደረጃ ተመልሷል። ብቁ ቀጣሪዎች በራስ-ሰር ተመዝግበዋል።
የጠፋ የደመወዝ እርዳታ (LWA)
LWA በኮቪድ-19 የተነሳ ከስራ ውጪ ለነበሩ እና የስራ አጥነት ጥቅማጥቅሞችን ለሚያገኙ ሰዎች በሳምንት ተጨማሪ $300 የሚሰጥ ጊዜያዊ የአደጋ ጊዜ መርሃ ግብር ነበር። የLWA ጥቅማጥቅሞች ከጁላይ 26፣ 2020 እስከ ሴፕቴምበር 5፣ 2020 ድረስ ይገኛሉ።
ድብልቅ የስራ አጥነት ካሳ (MEUC)
MEUC በቀጣይነት ያላው የእርዳታ ህግ የተፈጠረ ፕሮግራም ነበር። በሴፕቴምበር 4፣ 2021 ጊዜው አልፎበታል። ለ"ድብልቅ ሰራተኞች" ተጨማሪ $100 ሳምንታዊ ጥቅም ሰጥቷል። "ድብልቅ ሰራተኛ" ማለት ከቀጣሪ W-2 የሚቀበል እና የግል ስራ ገቢ የሚያገኝ ነው።
የወረርሽኝ የድንገተኛ ጊዜ የስራ አጥነት ካሳ (PEUC)
PEUC የመደበኛው የስራ አጥነት መድን ጥቅማጥቅሞቻቸው ላለቀባቸው ሰዎች የጥቅማጥቅም ማስፋፊያ ፕሮግራም ነበር። ፕሮግራሙን የፈጠረው የኮሮናቫይረስ እርዳታ፣ እፎይታና የኢኮኖሚ ደህንነት ህግ ነው። ፕሮግራሙን የፈጠረው የኮሮናቫይረስ እርዳታ፣ እፎይታና የኢኮኖሚ ደህንነት ህግ ነው።
የክፍያ ቼክ ጥበቃ ፕሮግራም (PPP)
PPP አነስተበኛ ንግዶች ሰራተኞቻቸውን በደመወዝ መዝገብ ላይ እንዲያቆዩ ለማበረታታት የተነደፈ የፌዴራል ብድር ነበር። ተበዳሪዎች ለPPP ብድር ምህረት ብቁ ነበሩ።
የወረርሽኝ የስራ አጥነት እርዳታ (PUA)
PUA ለኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምላሽ የተፈጠረ የፌዴራል የስራ አጥነት ጥቅማጥቅም መርሃ ግብር ነበር። በግል ስራ ለሚተዳደሩ ሰዎች፣ የኮንትራት ሰራተኞች ለሆኑ ሰዎች እና ሌሎች ለመደበኛ የስራ አጥነት ጥቅማጥቅሞች ብቁ ላልሆኑ ሰራተኞች የተዘጋጀ ነበር። አመልካቾች እስከ ሴፕቴምበር 4፣ 2021 ድረስ እስከ የPUA 79 ሳምንታት ድረስ ማግኘት ይችላሉ። ስለዚህ መርሃ ግብር ጥቅማጥቅሞች ተጨማሪ ዝርዝሮች በPUA ጥቅማጥቅሞች ካልኩሌተር፣ በPUA የራስ ስራ/ስራ መስተጋብራዊ መሳሪያ እና PUA Backdating Interactive Tool ውስጥ ይገኛሉ።
እንደ ስራ አጥ የሚያስቆጥሩ ልዩ ሁኔታዎች
በአጠቃላይ፣ ሰዎች በሳምንት ከ40 ሰዓት በታች ከሰሩ እና ከሳምንታዊ የጥቅማጥቅም መጠን (WBA) ያነሰ ገቢ ካገኙ ስራ አጥ እንደሆኑ ተደርገው ይቆጠራሉ። በ 2020 እና 2021 ውስጥ ያሉ ህጎች ሰዎች ከ WBA የበለጠ ገቢ ማግኘት አይችሉም ከሚለው ሁኔታ ለጊዜው የታገዱ እና ምንም አገልግሎት በማይሰጡበት ወይም በማንኛውም ሳምንት ውስጥ ከሙሉ ጊዜ ያነሰ ስራ ያጡ ሰዎች እንደ ሥራ አጥ እንደሆኑ ይቆጠራሉ። እነዚህ ልዩ ሁኔታዎች ከሴፕቴምበር 6፣ 2020 እስከ ጃንዋሪ 1፣ 2022 ድረስ በስራ ላይ ነበሩ።
የስራ አጥነት መጠበቂያ ሳምንት ማቋረጫ
የመጠበቂያ ሳምንት አንድ ሰው ሳምንታዊ የይገባኛል ጥያቄ የሚያቀርብበት እና ሁሉንም የብቃት መስፈርቶች የሚያሟላበት የመጀመሪያው ሳምንት ነው። ሰዎች ጥቅማጥቅሞችን መቀበል ከመጀመራቸው በፊት፣ የኦሪገን ህግ በየየይገባኛል ጥያቄው አንድ የመጠባበቂያ ሳምንት ይጠይቃል። በኤፕሪል 2020፣ አገረ ገዢ የኬት ብራውን ለኮቪድ-19 የአደጋ ጊዜ ጊዜ ሰራተኞቻቸው የሚጠብቀውን ሳምንት እንዲያገለግሉ የሚጠይቀውን መስፈርት አቋርጠዋል። አገረ ገዢዋ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ካወጁ በኋላ የመጀመሪያ የይገባኛል ጥያቄ ያቀረቡ ሁሉም ሰራተኞች ለተጠባባቂው ሳምንት ክፍያ ተቀበሉ። ይህ የይገባኛል ጥያቄው ላይ የአንድ ሳምንት ጥቅማጥቅሞችን አልጨመረም፣ ይልቁንም ሰራተኞች የመቆያ ሳምንት ካለበት ጊዜ ቀድሞ በሳምንት ውስጥ የመጀመሪያ ጥቅማ ጥቅሞችን እንዲያገኙ ፈቅዷል። እስከ ሴፕቴምበር 4፣ 2021 ድረስ አዲስ የይገባኛል ጥያቄ ያቀረቡ ሁሉም ሰዎች ለዚህ የመጀመሪያ ሳምንት ተከፍሏቸዋል።