ለሥራ አጥነት መድን ጥቅማጥቅሞች እንዴት ማመልከቻ እንደሚቀርብ

ለሥራ አጥነት መድን ጥቅማጥቅሞች የማመልከት ሂደት በርካታ ደረጃዎች አሉት፡፡ ሰነዶችን እና መረጃዎችን መሰብሰብ፣ የመጀመሪያ የይገባኛል ጥያቄ ማቅረብ እና ሳምንታዊ የይገባኛል ጥያቄዎችን ማቅረብን ያካትታል። እርስዎ ደግሞ መሥራት መቻል፣ ለሥራ ዝግጁ መሆን እና ሥራን በንቃት መፈለግ አለብዎት ። ከዚህ በታች ለስራ አጥነት መድን ስለማመልከት የበለጠ ይወቁ እና ስለ ብቁነት እና የይገባኛል ጥያቄ ሂደት ተጨማሪ ዝርዝሮችን በሥራ አጥ መድን የይገባኛል ጥያቄ መጽሄት ያግኙ፡፡

Marquam Bridge crosses the Willamette River as the sun sets behind the skyline of Portland.

ለጥቅማጥቅሞች ከማመልከትዎ በፊት

የማመልከቻውን ሂደት ከመጀመርዎ በፊት ሰነዶችዎን እና መረጃዎን ይሰብስቡ፡፡ ለስራ አጥነት መድን (UI) ጥቅማጥቅሞች የሚከተሉት ነገሮች ያስፈልጉዎታል፣

  • ስምዎ፣ የማህበራዊ ዋስትና ቁጥር፣ የልደት ቀን እና አድራሻ
  • የዩኤስ አሜሪካ ዜጋ ወይም የCOFA ደሴት ሰው ካልሆኑ፣ የእርስዎን USCIS ቁጥር፣ A-ቁጥር ወይም I-94 ቁጥር መጠቀም ይችላሉ።
  • የሚከተሉትን ጨምሮ፣ ያለፉት 18 ወራት ሙሉ የስራ ታሪክዎ፣
  • የአሰሪ ስም(ዎች)
  • የአሰሪ አድራሻ(ዎች)
  • የአሰሪ ስልክ ቁጥር(ዎች)
  • ለእያንዳንዱ አሰሪ ወይም ቀጣሪ የስራዎ መጀመሪያ እና ማብቂያ ቀናት

ጥቅማጥቅሞችዎ በቀጥታ በባንክ እንዲተላለፍ መመዝገብ ከፈለጉ የባንክ ሂሳብ ቁጥርዎ እና ራውትንግ ቁጥርዎ

ለጥቅማጥቅሞች ማመልከት

ደረጃ 1 የመጀመሪያ የይገባኛል ጥያቄ ያስገቡ

የማመልከቻው ሂደት የመጀመሪያ እርምጃ የመጀመሪያ የይገባኛል ጥያቄ ማቅረብ እና ለስራ አጥነት ጥቅማጥቅሞች ብቁ መሆንዎን ማወቅ ነው።

የመጀመሪያ የይገባኛል ጥያቄ የሚያቀርቡት በጥቅማጥቅም አመት አንድ ጊዜ ብቻ ነው (ያቀረቡት የ52-ሳምንት ክፍለ ጊዜ መጀመሪያ ያስገቡት ሳምንት)። ማመልከቻ ለማቅረብ በርካታ መንገዶች አሉ፡-

  • በኦንላይን initial claim ያስገቡ፦ ለማመልከት ፈጣኑ መንገድ በFrances Online በኩል ነው። በኦንላይን ማመልከቻውን ይሙሉ እና ሁሉንም አስፈላጊ መረጃዎች ያቅርቡ፡፡

    ይህ ስርዓት እንደ አድራሻዎን ማዘመን እና በቀጥታ ክፍያው በባንክ እንዲተላለፍ እንዲመዘገቡ የመሳሰሉ ነገሮችን እንዲያደርጉ ይፈቅድልዎታል.

    መረጃዎን በማመልከቻዎ ላይ በትክክል ማስገባትዎን ያረጋግጡ! አንዴ የይገባኛል ጥያቄ ካቀረቡ በኋላ ለውጦችን ማድረግ አይችሉም። ስህተት ከሰሩ ገንዘብዎ በቀናት ወይም በሳምንታት ሊዘገይ ይችላል። በማህበራዊ ዋስትና ቁጥርዎ እና በአድራሻዎ ላይ ጥንቃቄ ያድርጉ።

  • የመጀመሪያ የይገባኛል ጥያቄ በስልክ ያቅርቡ፡ 1-877-File-4-UI (1-877-345-3484) በመደወል በስልክ ማመልከት ይችላሉ። የሚፈልጉትን ቋንቋ ለወኪላችን ያሳውቁን። ከሁለት ቋንቋ ተናጋሪ ወይም ነፃ አስተርጓሚ ጋር ያገናኙዎታል። እንዲሁም የእርስዎን ስም፣ የተጠየቀው ቋንቋ፣ ስልክ ቁጥር እና ጥሪ ለመቀበል የተሻለ ጊዜ በኢሜይል ለእኛ የቋንቋ ተደራሽነት ቡድን በቋንቋዎ መልሶ ጥሪ ለመቀበል መላክ ይችላሉ።

    በስልክ ካመለከቱ የሚያጋጥሙዎት የማቆያ ጊዜዎች እንደደወሉበት ቀን እና ሰዓት ይለያያሉ።

  • የመጀመሪያ የይገባኛል ጥያቄ ያስገቡ፣ የኦንላይን ወይም የስልክ አማራጮችን መጠቀም ካልቻሉ፣ የመጀመሪያ የይገባኛል ጥያቄን በቅጽ 115 ማስገባት ይችላሉ። ቅጹ የተጠናቀቀውን ቅጽ በፋክስ በመላክ ወይም በፖስታ ቤት መላክ ላይ መመሪያ አለው።

የመጀመሪያ የይገባኛል ጥያቄ ካቀረቡ በኋላ፣ ማመልከቻዎ እንደደረሰን እናሳውቅዎታለን።

Frances Online በኩል የስራ አጥ ማመልከቻ ሲያስገቡ የማረጋገጫ ኢሜይል ይደርስዎታል። ይህ ኢሜይል ማመልከቻዎ እንደደረሰን ያረጋግጣል። በስልክ ካመለከቱ፣ የይገባኛል ጥያቄዎ እንደደረሰ ተወካያችን ያሳውቅዎታል።

ለስራ አጥነት ኢንሹራንስ ጥቅማጥቅሞች ብቁ መሆንዎን እና ሳምንታዊ የይገባኛል ጥያቄዎችዎን ካስገቡ እና ሌላ ብቁ ከሆኑ ምን ያህል ገንዘብ ማግኘት እንደሚችሉ የሚገልጽ ደብዳቤ በፖስታ ይደርሰዎታል። ቀጥሎ ምን ማድረግ እንዳለብዎት የሚጠቁም ደብዳቤም ይደርስዎታል። ብቁ ካልሆኑ፣ ለምን እንደማይችሉ ደብዳቤው ይነግርዎታል።

አብዛኛዎቹ ማመልከቻዎች በአንድ ሳምንት ውስጥ ይገመገማሉ። የይገባኛል ጥያቄዎን ሲልኩልን ስህተት ከሰሩ፣ ከእርስዎ ተጨማሪ መረጃ እስክንቀበል ድረስ የማመልከቻዎን ሂደት ሊያዘገይ ይችላል።

claim statusን በFrances Online ውስጥ ማረጋገጥ ይችላሉ።

ደረጃ 2 ሳምንታዊ የይገባኛል ጥያቄዎችን ፋይል ያድርጉ

ብቁ ከሆኑ ጥቅማ ጥቅሞችን መቀበል ለመጀመር፣ እንዲሁም በየሳምንቱ የይገባኛል ጥያቄዎችን ማቅረብ አለብዎት። ሳምንታዊ የይገባኛል ጥያቄዎች ከመጀመሪያው የይገባኛል ጥያቄ የተለዩ ናቸው። ገንዘብዎን ለማግኘት ሁለቱንም የመጀመሪያ የይገባኛል ጥያቄ እና ሳምንታዊ የይገባኛል ጥያቄዎችን ማስገባት ያስፈልግዎታል፣ እና የመጀመሪያ የይገባኛል ጥያቄዎን ለማፅደቅ አሁንም እየጠበቁ ቢሆንም ሳምንታዊ የይገባኛል ጥያቄዎችዎን ማስገባት አለብዎት።

ሳምንታዊ የይገባኛል ጥያቄ ለዚያ ሳምንት ምን ያህል ገንዘብ እንደምንልክልዎ ይወስናል። አንድ ሳምንት ከእሁድ እስከ ቅዳሜ ነው። ቅዳሜ ለተጠናቀቀው ሳምንት የይገባኛል ጥያቄዎን ለማቅረብ እስከ እሁድ ድረስ መጠበቅ አለብዎት።

ጥቅማጥቅሞችን ማግኘትዎን ለመቀጠል በየሳምንቱ ሳምንታዊ የይገባኛል ጥያቄ ማቅረብ ያስፈልግዎታል። በዚያ ሳምንት ብሠሩም ሳምንታዊ ጥያቄ ያስገቡ። በዚያ ሳምንት ለሰሩት ለማንኛውም ስራ ሰአትዎንና እና ገቢዎን ማሳወቅ አለብዎት። በማንኛውም ሳምንት ከ40 ሰአት በታች ሰርተውና ከሳምንታዊ ጥቅማጥቅምዎ ያነሰ ገቢ አግኝተው ከሆነ ስራ አጥ እንደሆኑ ይቆጠራሉ ።

እንደገና፣ የመጀመሪያ የይገባኛል ጥያቄዎ ተቀባይነት ማግኘቱን ለመስማት አሁንም እየጠበቁ ቢሆንም ሳምንታዊ የይገባኛል ጥያቄዎችዎን ማስገባት አለብዎት። ተቀባይነት ካገኘ፣ ለእነዚያ ሳምንታት ሳምንታዊ የይገባኛል ጥያቄዎችዎን ካቀረቡ ላለፉት ሳምንታት ሁሉ ገንዘብ እንልክልዎታለን።

ደረጃ 3 ወደ ሥራ ለመመለስ ዝግጁ ይሁኑ

የሥራ አጥነት ጥቅማ ጥቅሞችን የሚያገኙ ሰዎች ሥራ መፈለግ እና ፍለጋቸውን መመዝገብ አለባቸው። እርስዎ ደግሞ መሥራት መቻል፣ ለሥራ ዝግጁ መሆን እና ሥራን በንቃት መፈለግ አለብዎት ። እንዲሁም፣ iMatchSkills.org ላይ የስራ ፈላጊ ፕሮፋይል መመዝገብ እና መሙላት ሊያስፈልግዎ ይችላል፡፡ እና በወርክሶርስ የኦሬገን ማዕከል ( WorkSource Oregon center ) በአከባቢዎ የእንኳን ደህና መጣችሁ ውይይትን ያጠናቅቁ ፡፡

እርዳታ ያስፈልግዎታል?

በተደጋግሞ የሚነሱ ጥያቄዎች ወይም በድረ-ገጻችን በመፈለግ ለብዙ ጥያቄዎች መልስ ማግኘት ይቻላል፡፡ እርዳታ ወይም መረጃ ለማግኘት ለሌሎች መንገዶች እኛን ለማግኘት መንገዶች መረጃ ገጽ ይጎብኙ፡፡

ለውጦችን ማድረግ

አንዴ የይገባኛል ጥያቄ ካቀረቡ በኋላ፣ በርሱ ላይ ለውጦችን ማድረግ አይችሉም። የይገባኛል ጥያቄዎን በሚሞሉበት ጊዜ ሁሉንም መረጃዎች በትክክል ማስገባትዎ አስፈላጊ ነው መረጃን በተሳሳተ መንገድ ማስገባት ጥቅማጥቅሞችን ያዘገያል።

"I Want To... Manage Names and Addresses" የሚለውን አማራጭ በመምረጥ አድራሻዎን በFrances Online ማዘመን ይችላሉ። አድራሻዎን በኦንላይን ላይ ማዘመን ካልቻሉ ወይም በይገባኛል ጥያቄዎ ላይ ሌላ እርዳታ ከፈለጉ እባክዎን በኛ " ያግኙን ቅጽ" ( Contact Us form ) በኩል ትኬት ያስገቡ ወይም በ1-877-File-4-UI (1-877-345-3484) ይደውሉልን።