ወርክሼር ምንድን ነው?

የወርክሼር ፕሮግራም የኦሬገን የንግድ ድርጅቶች ከሥራ ማባረርን እንዲቆጠቡ እና በጊዜያዊ የንግድ ሥራ ማሽቆልቆል ወቅት ጎበዝ ሠራተኞችን እንዲያስቀጥሉ ያግዛል። አሠሪዎች ሠራተኞችን ከማሰናበት ይልቅ፣ የአንዳንድ ሠራተኞችን ሰዓት ይቀንሳሉ ከዚያም እነዚህ ሠራተኞች በሰዓታቸው መቆረጥ ምክንያት የሚያጡትን የተወሰነውን የደመወዝ ክፍያ የሥራ አጥነት ኢንሹራንስ ጥቅማጥቅሞችን በመጠቀም ያካክሳሉ።

ወርክሼር አማካይነት፣ አሠሪዎች ከሥራ መባረርን ያስወግዳሉ፣ የሰለጠኑ እና ከፍተኛ ችሎታ ያላቸው ሰራተኞቻቸውን ያስቀምጣሉ፣ አዳዲስ ሰራተኞችን ከመቅጠር እና ከማሰልጠን ይቆጠባሉ፣ የሰራተኞችን ሞራል ለመጠበቅ ይረዳሉ፡፡ ይህም ሰራተኞች ተጨማሪ የስራ ዋስትና እንዲኖራቸው፣ ችሎታቸውን እና ብቃታቸውን እንዲጠብቁ፣ የጤና አጠባበቅ እና የጡረታ ጥቅማጥቅሞችን እንዲጠብቁ እና የሳምንት የይገባኛል ጥያቄዎችን ሳያቀርቡ የስራ አጥነት ኢንሹራንስ ጥቅማጥቅሞችን እንዲያገኙ ያስችላቸዋል።

በመቶዎች የሚቆጠሩ ቀጣሪዎች ከሥራ መባረርን ለማስወገድ በኦሬገን ውስጥ ወርክሼርን ይጠቀማሉ።

በወርክሼር እቅድ የሚሸፈኑ ሰራተኞች ሰዓታቸው ቢያንስ በ20% መቀነስ ግን ከ 40% ያልበለጠ፣ ለስራ ዝግጁ መሆን እና ለቀጣሪው የሙሉ ጊዜ ስራ በተከታታይ ለስድስት ወራት ወይም በትርፍ ሰዓት አንድ ዓመት የሰሩ መሆን አለባቸው። እንዲሁም በወርክሼር እቅድ የተሸፈኑ ሰራተኞች ወቅታዊ ሰራተኞች ሊሆኑ አይችሉም፡፡

የወርክሼር ዕቅዶች እስከ አንድ ዓመት ድረስ ይቆያሉ። አንድ ሰራተኛ ለዚያ ቀጣሪ ለመስራት ከዚያ ወዲያ የማይገኝ ከሆነ የሥራ መምሪያ ብቁነትን ይገመግማል።

ስለ ወርክሼር ፕሮግራም የበለጠ መረጃ ለማግኘት በ 503-947-1800 ይደውሉ ወይም ወርክሼርን (Work Share page) በኦሬገን የሥራ መምሪያ ድረ ገጽ ላይ ይጎብኙ ፡፡

ጥያቄዎች አሉዎት?

ስለ ወርክሼር ፕሮግራም የበለጠ መረጃ ለማግኘት በ 503-947-1800 ይደውሉ ወይም ወርክሼርን (Work Share page) በኦሬገን የሥራ መምሪያ ድረ ገጽ ላይ ይጎብኙ ፡፡

Work Share page