እኛ የምንገኝባቸው መንገዶች

ብዙ ሰዎች ለመኖሪያ፣ ለምግብ እና ለሌሎች መሰረታዊ ወጪዎች በስራ አጥነት መድን ጥቅማጥቅሞች ላይ እንደሚተማመኑ እና ስለ ስራ አጥነት ሂደት ጥያቄዎች ሊኖራቸው እንደሚችል እና በፍጥነት መልስ እንደሚያስፈልጋቸው እናውቃለን። ለብዙ ጥያቄዎች መልሶች በእኛ ተደጋግሞ የሚነሱ ጥያቄዎች ውስጥ ይገኛሉ፡፡ መረጃ ወይም እርዳታ ለማግኘት ሌሎች መንገዶች ከዚህ በታች አሉ።

The Bridge of the Gods spans the Columbia River at Cascade Locks. The mountains of Oregon rise in the background.

በእኛ የኦንላይን የይገባኛል ጥያቄ ስርዓት በኩል የይገባኛል ጥያቄን ያስገቡ ወይም ያረጋግጡ

የመጀመሪያውን የይገባኛል ጥያቄዎን ለማቅረብ እና ያቀረቡትን የይገባኛል ጥያቄ ለማየት ምርጡ መንገድ የእኛን የኦንላይን ላይ የይገባኛል ጥያቄ ( Online Claim System ) ስርዓት በመጠቀም ነው ፡፡ ይህ ስርዓት እንደ አድራሻዎን ማዘመን እና በቀጥታ ተቀማጭ ገንዘብ እንዲመዘገቡ የመሳሰሉ ነገሮችን እንዲያደርጉ ይፈቅድልዎታል፡፡ የኦንላይን የይገባኛል ጥያቄ ስርዓት በአሁኑ ጊዜ በእስፓኒኛና በእንግሊዝኛ ይገኛል።

የይገባኛል ጥያቄ በሚያስገቡበት ጊዜ ሁሉንም መረጃዎች በትክክል ማስገባት አስፈላጊ መሆኑን ልብ ይበሉ፣ ምክንያቱም የይገባኛል ጥያቄዎን በኦንላይን የይገባኛል ጥያቄ ስርዓት ከላኩልን በኋላ ለውጦችን ማድረግ አይችሉም፡፡ የተሳሳተ መረጃ ማስገባት ጥቅማጥቅሞችን ያዘገያል፣ ስለዚህ መረጃን እንዴት እንደሚያስገቡ በትኩረት ይከታተሉ።

የእኛን "ያግኙን" ቅጽ በመጠቀም ትኬት ይላኩ።

ስለ ሥራ አጥነት ጥቅማጥቅሞች ለሚነሱ ጥያቄዎች የቲኬት አሰጣጥ ስርዓትን እንጠቀማለን። የሚፈልጉትን መረጃ በኦንላይን ማግኘት ካልቻሉ ወይም አሁንም ለልዩ ባለሙያ ጥያቄዎች ካሉዎት እባክዎን በእኛ ያግኙን ቅጽ በኩል ቲኬት በመላክ ያግኙን፡፡

እንዲሁም የሚከተሉትን ለማድረግ ወደዚህ ትኬት መላክ ይችላሉ፡-

  • ሰነዶችን በኦንላይን መቀበያ ላይ ለመጫን ( አፕሎድ ) ለማድረግ
  • ለጥያቄዎ የጎደለ ወይም የተስተካከለ መረጃ
  • ለችሎት ለመጠየቅ ወይም ለይግባኝ ለማመልከት

በእኛ "ያግኙን" ቅጽ ውስጥ ትኬት ሲያስገቡ የሚመርጡትን ቋንቋ መምረጥ ይችላሉ።

በስልክ እርዳታ ያግኙ

የኢንተርኔት አገልግሎት ከሌለዎት ወይም በአንዱ የኦንላይን የግንኙነት አማራጮቻችን ላይ ችግር ካጋጠመዎት ወይም ልዩ ባለሙያተኛ የሚፈልግ ውስብስብ ችግር ካለብዎ በተጨማሪ በ1-877-File-4-UI (1-877-345-3484) በመደወል እርዳታ ማግኘት ይችላሉ ። የስልክ ሰአታችን ከጧቱ 8 ሰአት እስከ ምሽቱ 5፡30 ሰአት ነው።

የሚፈልጉትን ቋንቋ ለወኪላችን ያሳውቁን። ከሁለት ቋንቋ ተናጋሪ ወይም ነፃ አስተርጓሚ ጋር ያገናኙዎታል። እንዲሁም የእርስዎን ስም፣ የተጠየቀው ቋንቋ፣ ስልክ ቁጥር እና ጥሪ ለመቀበል የተሻለ ጊዜ በኢሜይል ለእኛ የቋንቋ ተደራሽነት ቡድን በቋንቋዎ መልሶ ጥሪ ለመቀበል መላክ ይችላሉ

በስልክ ከመደበኛ የስራ ሰዓታችን ውጭ በመደወል በይነተገናኝ የድምጽ ምላሽ ስርዓታችንን በመጠቀም የመጀመሪያ የይገባኛል ጥያቄ መጀመር ወይም ሳምንታዊ ጥቅማጥቅሞችን ማስገባት ይችላሉ።

የይገባኛል ጥያቄ ባለሙያን ማነጋገር ከፈለጉ በጊዜ ጧት እና በጊዜ ከሰአት በኋላ ለመደወል በጣም ጥሩ ጊዜ ናቸው። የመመለሻ ጥሪዎችን ቀጠሮ ማስያዝ አንችልም። የጥሪ መጠኖች ሰኞ እና አርብ ከፍተኛ ሲሆን የባንክ ወይም የፌደራል በዓል ሰኞ ላይ ከዋለ ራቡእ ላይ ከፍተኛ ሊሆን ይችላል።

ጥሪዎን ወደ ትክክለኛው የይገባኛል ጥያቄ ባለሙያ ለማድረስ ምናሌውን በጥንቃቄ ማዳመጥዎን እና ትክክለኛውን አማራጭ ይምረጡ።

ወደ እርስዎ መደወል ስንፈልግ፣ በእርስዎ የደዋይ መታወቂያ ላይ እንደ ታገደ ስልክ ቁጥር ሊያሳይ ከሚችል ካልተዘረዘረ መስመር እንጠራለን። ከኦኢዲ መልስ በስልክ ለመስማት የምጠባበቁ ከሆነ ስልክዎ ከታገዱ ቁጥሮች የሚመጡ ጥሪዎችን መቀበሉን እና በድምጽ መልእክትዎ ላይ መልእክት እንድንተውልዎት ቦታ እንዳለ ያረጋግጡ። በድምጽ መልእክትዎ ላይ መልእክት መተው ካልቻልን ደብዳቤ እንልካለን።

የእኛን የውይይት መሣሪያ (Chat Tool) ይጠቀሙ

እንዲሁም ምናባዊ ረዳት ወይም የውይይት መሳሪያ እናቀርባለን። በእያንዳንዱ የድረ-ገፃችን ገፅ ቀኝ ጥግ ከታች ባለው ሰማያዊ ክብ ላይ ጠቅ ያድርጉ። ይህ መሳሪያ ከስራ አጥነት ጋር በተያያዙ መሰረታዊ ጉዳዮችን ለመፍታት ከሚፈልጉት መረጃ ጋር ሊያገናኝዎት እና እንዲሁም የይገባኛል ጥያቄ ሁኔታን በተመለከተ እርዳታ ከጥያቄ ባለሙያ ጋር ሊያገናኝዎት እና የክፍያ ጉዳዮችን መጠየቅ ይችላል።

ቻት ( ውይይት) በሚፈልጉበት ቋንቋ የማይገኝ ከሆነ፣ ቨርቹዋል ( ምናባዊ) ረዳቱ የምንገናኝበትን ስልክ ቁጥር እና የኢሜል አድራሻ ይሰጥዎታል፣ የሚፈልጉትን ቋንቋ ያሳውቁን እና እኛ ከሁለት ቋንቋ ተናጋሪ ተወካይ ወይም ነፃ አስተርጓሚ ጋር እናገናኝዎታለን።

እርዳታ ያስፈልጋል?

የኦሬጎን የሥራ መምሪያ (Oregon Employment Department (OED)) ለሁሉም በእኩልነት ዕድል ሰጭ ድርጅት ነው። አገልግሎቶቻችንን መጠቀም እንድችሉ OED ነፃ እርዳታ ይሰጣል። አንዳንድ ምሳሌዎች የምልክት ቋንቋ እና የንግግር ቋንቋ አስተርጓሚዎች፣ ጽሑፎች በሌሎች ቋንቋዎች፣ ጎላ ትልቅ ህትመት፣ ኦዲዮ (ድምጽ) እና ሌሎች ቅርጸቶች ናቸው። እርዳታ ከፈለጉ፣ እባክዎን ወደ unemployment.oregon.gov ይሂዱ እና ያግኙን (Contact Us) የሚለውን ጠቅ ያድርጉ ወይም በ 877-345-3484 ይደውሉልን፡፡ መስማት የተሳናቸው (የTTY ተጠቃሚዎች 711 ይደውሉ።

Contact Us

ለኢሜል ዝመናዎች ይመዝገቡ

የሥራ መምሪያ ስለ ፕሮግራሞቹ ወቅታዊ መረጃዎችን በኢሜል እንዲልክልዎ ይፈልጋሉ?