የስራ አጥነት መድን ህጎች እና ደንቦች

በዚህ ገጽ ላይ:

ታሪክ

በ 1935 እና ለታላቁ የኢኮኖሚ ድቀት ምላሽ፣ ኮንግረስ እንደ የማህበራዊ ዋስትና ህግ (SSA) አካል የሆነ የስራ አጥነት መድን ፕሮግራም አወጣ። ዛሬ ላይ፣ ፕሮግራሙ ከዩኤስ የሰራተኛ መምሪያ ክትትል ጋር የፌዴራል-ስቴት ሽርክና ነው። ማህበራዊ ዋስትና ህግ የስራ አጥነት መድን ህግ ላላቸው ስቴቶች የስራ አጥነት መድንን ለማስተዳደር እና የጥቅማ ጥቅም ክፍያዎችን ለመቆጣጠር የፌዴራል መስፈርቶችን የሚያሟሉ ድጎማዎችን ይሰጣል። ስቴቶች ይህንን የፌዴራል ፈንድ መጠቀም የሚችሉት ለስራ አጥነት መድን ፕሮግራሞች አስተዳደር ብቻ ነው።

እያንዳንዱ ስቴት የራሱ የስራ አጥነት መድን ፕሮግራም አለው። ከፌዴራል መስፈርቶች ጋር ለማስማማት የተነደፈው የስቴት ድንጋጌ፣ ስቴት የሚሰጠውን የስራ አጥነት ጥቅማጥቅሞች እንዲሁም ሰራተኞች እንዴት እና መቼ ብቁ እንደሆኑ ይዘረዝራል። እንዲሁም ድንጋጌው በስቴቱ ውስጥ ያሉ አሰሪዎች ለስቴቱ የስራ አጥነት መድን መተማመኛ ፈንድ የሚከፍሉትን የግብር መዋጮ ያቋቁማል።

የኦሪገን የቅጥር መምሪያ የኦሪገንን የስራ አጥነት መድን ፕሮግራም ያስተዳድራል። በኦሪገን ስቴት ህግ አውጭዎች ውስጥ በኦሪገን የተሻሻለው ህግ 657 ውስጥ ያሉትን የስራ አጥነት መድን ህጎች ይጽፋሉ።

የኦሪገን ስቴት ኤጀንሲዎች ህጋዊ ስልጣናቸውን ተግባራዊ ለማድረግ እና ለመተርጎም የሚረዱ አስተዳደራዊ ደንቦችን ይፈጥራሉ። የኦሪገን የቅጥር መምሪያ ደንቦች በኦሪገን አስተዳደራዊ ድንቦች ምዕራፍ 471 ውስጥ ይገኛሉ። እነዚህም ለስራ አጥነት መድን ፕሮግራም ደንቦችን ያካትታሉ። አንዳንድ ጊዜ፣ የኦሪገን የቅጥር መምሪያ አዲስ የታቀዱ ወይም ጊዜያዊ ደንቦችን ያዘጋጃል።

በተጨማሪም ደግሞ፣ በኦሪገን እና በፌደራል ደረጃ ያሉ የህግ አውጭዎች በኦሪገን የስራ አጥነት መድን ፕሮግራም ላይ ለውጦችን ሊያደርጉ ይችላሉ። ለምሳሌ ያህል፣ የኦሪገን የቅጥር መምሪያ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት በርካታ የፌዴራል እና የስቴት ህግ አውጪ በወሰዷቸው እርምጃዎች የተነሳ በርካታ አዳዲስ የፌዴራል ፕሮግራሞችን እና የዘመኑን የስቴት መስፈርቶችን ተግባራዊ አድርጓል።