የይገባኛል ጥያቄዬን ካስገባሁ በኋላ ምን ይከሰታል?
ከሥራ አጥነት የመድን ፕሮግራም የሚሰጡ ጥቅማጥቅሞችን ለማግኘት ማመልከቻ ማቅረብ፣ የመጀመሪያ የይገባኛል ጥያቄ በመባልም ይታወቃል፣ አስፈላጊ የመጀመሪያ እርምጃ ነው። በመቀጠል፣ ጥቅማጥቅሞችን ለማግኘት ብቁ ለመሆን የተወሰኑ ስራዎችን ማጠናቀቅ አለብዎት።
- ከእነዚህ ተግባራት መካከል አንዳንዶቹ በተወሰኑ የጊዜ ገደቦች መጠናቀቅ አለባቸው።
- እንደ ሳምንታዊ የይገባኛል ጥያቄዎች እና የሥራ ፍለጋ ያሉ አንዳንድ ሥራዎች ጥቅማጥቅሞችን ለማግኘት የሚፈልጉ ከሆነ፣ በየሳምንቱ መጠናቀቅ አለባቸው።
እነዚህን ተግባራት ካላጠናቀቁ ጥቅማጥቅሞችዎን ልንከለክል እንችላለን። ከእኛ መረጃ ለማግኘት የፖስታ ሳጥንዎን፣ ኢሜይልዎን እና የFrances Online መለያዎን በየጊዜው ይፈትሹ።
ምን ማድረግ አለብኝ?
በየሳምንቱ፣ ለጥቅማጥቅሞች ብቁ ለመሆን የተወሰኑ ተግባራትን ማጠናቀቅ አለብዎት፦
- አብዛኛዎቹ የይገባኛል ጥያቄ አቅራቢዎች ለጥቅማጥቅሞች ብቁ ለመሆን ሥራ መፈለግ አለባቸው።
- ብቁ መሆንዎን ለማሳየት ሳምንታዊ የይገባኛል ጥያቄ ማቅረብ አለብዎት።
- በሳምንታዊ የይገባኛል ጥያቄዎች ገጽ ላይ ተጨማሪ ይወቁ።
ብቁ ለመሆን ማጠናቀቅ ያለብዎት ሌሎች ተግባራትም አሉ። እነዚህን ተግባራት አንድ ወይም ከዚያ በላይ ጊዜ እንዲያከናውኑ ሊጠየቁ ይችላሉ። በFrances Online እና በደብዳቤዎች እናሳውቅዎታለን። የሚከተሉትን ማወቅ ሊኖርብዎ ይችላል፦
- ማንነትዎን ያረጋግጡ። መረጃዎን እና ጥቅማጥቅሞችዎን እንጠብቃለን። ማንነትዎን ያረጋግጡ ገጽ ላይ ተጨማሪ ይወቁ።
- ከWorkSource Oregon የሥራ ስምሪት ባለሙያ ጋር ይገናኙ። በስራ ፍለጋ እና በWorkSource Oregon ገጽ ላይ ተጨማሪ ይወቁ።
- ለጥቅማጥቅሞች ብቁ መሆንዎን ለመወሰን የሚያስፈልጉ መረጃዎች ላይ ላሉ ጥያቄዎቻችን ምላሽ ይስጡ።
Frances Online እና ደብዳቤዎን በመደበኛነት ያረጋግጡ እና ወዲያውኑ ምላሽ ይስጡ ወይም ጥቅማጥቅሞችዎን ልንከለክል እንችላለን። ተግባራት የማብቂያ ቀናት አሏቸው። የሁኔታ መልዕክቶች ገጽ ላይ ተጨማሪ ይወቁ።
የደመወዝ እና ሊሆኑ የሚችሉ ጥቅማጥቅሞች ሪፖርት
ማመልከቻውን ካቀረቡ በኋላ፣ የደመወዝ እና ሊሆኑ የሚችሉ ጥቅማጥቅሞች ሪፖርት እንልክልዎታለን። ይህ ትክክለኛ የይገባኛል ጥያቄ ካለዎት እና በመነሻ ዓመት ደመወዝዎ መሠረት ምን ያህል ገንዘብ ለመቀበል ብቁ እንደሆኑ ይነግርዎታል። በሪፖርቱ ውስጥ የተዘገበውን የእርስዎን ደመወዝ እና ሰዓታት በጥንቃቄ ይገምግሙ። መረጃው የተሳሳተ ከሆነ ማመልከቻዎን እንደገና እንድንገመግመው መጠየቅ ይችላሉ።
ደመወዝ ወይም ሰዓታት ከተጨመሩ ወይም ከተወገዱ፣ አዲስ የደመወዝ እና ሊሆኑ የሚችሉ ጥቅማጥቅሞች ሪፖርት ያገኛሉ። ይህ ዳግም መወሰን ይባላል።
እንዲሁም ሪፖርቱ የሚከተሉትን ያሳያል፦
- የእርስዎ ሳምንታዊ የጥቅማጥቅም መጠን። ይህም ሁሉንም መስፈርቶች ካሟሉ በየሳምንቱ ሊያገኙት የሚችሉት መጠን ነው።
- የእርስዎ ከፍተኛው የደመወዝ መጠን። ይህ በ52-ሳምንታት የይገባኛል ጥያቄዎ ወቅት ሊገኝ የሚችለው አጠቃላይ መጠን ነው፣ ይህም የእርስዎ የጥቅማጥቅም ዓመት በመባል ይታወቃል።
- የጥቅማጥቅም ዓመቱ የሚጀምርበት እና የሚያበቃበት ቀን። ጥቅማጥቅሞችን መጠየቅ የሚችሉት በእነዚህ ቀናት መካከል ባሉት ሳምንታት ውስጥ ብቻ ነው። ለጥቅማጥቅሞች ከጊዜው ማብቂያ በኋላ እንደገና ማመልከቻ ማቅረብ ይችላሉ።
- በመነሻ ዓመትዎ ውስጥ ተቀጥረው የሰሩላቸው አሰሪዎች። ይህ የሚያካትተው የOregon አሠሪዎችን ብቻ ሊሆን ይችላል። ስለ የእርስዎ የፌዴራል ቅጥር፣ የውትድርና ደመወዝ ወይም ከOregon ውጭ ስላሉ አሰሪዎችዎ መረጃ ለማግኘት ተጨማሪ ጊዜ ሊወስድብን ይችላል።
- የይገባኛል ጥያቄዎ መነሻ ዓመት ውስጥ አሠሪዎ እያንዳንዱን ሩብ እንደሰሩ ያቀረቡት ሪፖርት ውስጥ የተመዘገበው ደመወዝ እና ሰዓታት።
- ይህ መግለጫ የመጀመሪያ ውሳኔም ይሁን እንደገና መወሰን።
እንዲሁም ይህ ደብዳቤ ስለ የይገባኛል ጥያቄዎ ሌሎች መረጃዎችን ሊያቀርብ ይችላል። የሚከተለው ከሆነ ይነግርዎታል፦
- ለጥቅማጥቅሞች ትክክለኛ የይገባኛል ጥያቄ የለዎትም። የተመዘገበ ደመወዝ እጥረት ገጽ ላይ ተጨማሪ ይወቁ።
- የይገባኛል ጥያቄዎ ለመደበኛ ወይም ለአማራጭ የመነሻ ዓመት ነው (ተጨማሪ መረጃ ከዚህ በታች ይገኛል)።
ማመልከቻዬን ለመገምገም ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል?
የመጀመሪያዎቹን የይገባኛል ጥያቄዎች ለመገምገም፣ ስለ ብቁነት ውሳኔ ለመስጠት እና የደመወዝ እና ሊሆኑ የሚችሉ ጥቅማጥቅሞችን ሪፖርት ለእርስዎ ለመላክ ወደ ሦስት ሳምንታት ያህል ይወስዳል።
አንዳንድ የይገባኛል ጥያቄዎች ውስብስብ ከመሆናቸውም በላይ ለመገምገም ተጨማሪ ጊዜ ያስፈልጋቸዋል። በዳኝነት ገጽ ላይ ተጨማሪ ይወቁ።
ከሶስት ሳምንታት በላይ ለሚቆይ የመጠበቂያ ጊዜ አንዳንድ የተለመዱ ምክንያቶች እነሆ፦
- ሳምንታዊ የይገባኛል ጥያቄዎን ለማስገባት አንድ ሳምንት ወይም ከዚያ በላይ አሳልፈዋል። ይህ ጥቅማጥቅሞች መዘግየት በጣም የተለመደ ምክንያት ነው። ጥቅማጥቅሞችን መቀጠል ከፈለጉ በየሳምንቱ ሳምንታዊ የይገባኛል ጥያቄ ማቅረብ አለብዎት፣ ይህም ማመልከቻዎን ካስገቡ በኋላ ያለውን የይገባኛል ጥያቄዎን የመጀመሪያ ሳምንት ይጨምራል። አንድ ሳምንት ካሳለፉ፣ የይገባኛል ጥያቄዎን እንደገና ማስጀመር ይኖርብዎታል። የይገባኛል ጥያቄን እንደገና ማስጀመር ገጽ ላይ ተጨማሪ ይወቁ።
- በእርስዎ ሳምንታዊ የይገባኛል ጥያቄ ውስጥ ገቢዎን ሪፖርት አላደረጉም።
- ከውትድርና፣ ከፌደራል መንግስት ወይም በሌላ ግዛት ውስጥ በመስራት የሚያገኙት ገቢ ነበረዎት። ከስርዓቶቻቸው ምላሽ ለማግኘት ተጨማሪ ጊዜ ይወስዳል።
- የእርስዎ ጉዳይ ተጨማሪ ግምገማ ያስፈልገዋል። የእኛ የዳኝነት ባለሙያዎች ከእርስዎ፣ ከአሰሪዎ ወይም ከሌሎች ጋር ስለ ስራዎ ሁኔታ ወይም ገቢዎ መነጋገር አለባቸው።
ስለ የይገባኛል ጥያቄዎ ዝመናዎችን እና መጠይቆችን ለማግኘት Frances Online መፈተሽ ይችላሉ።
በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች
-
ሩብ ዓመት ምን ማለት ነው?
ዓመቱ በአራት የቀን መቁጠሪያ ሩብ ዓመታት ይከፈላል፦
- ሩብ ዓመት 1 (Q1)፦ ጃኑዋሪ፣ ፌብሩዋሪ እና ማርች
- ሩብ ዓመት 2 (Q2)፦ ኤፕሪል፣ ሜይ አንድ ጁን
- ሩብ ዓመት 3 (Q3)፦ ጁላይ፣ ኦገስት እና ሴፕቴምበር
- ሩብ ዓመት 4 (Q4)፦ ኦክቶበር፣ ኖቬምበር እና ዲሴምበር
-
የመነሻ ዓመት ምንድን ነው?
የእርስዎ መደበኛ የመነሻ ዓመት፣ የጥቅማጥቅምዎ አመት ከመጀመሩ በፊት፣ ካለፉት አምስት የተጠናቀቁ የቀን መቁጠሪያ ሩብ ዓመታት የመጀመሪያዎቹን አራት ሩብ ዓመታት ያካትታል። የጥቅማጥቅም ዓመትዎ የመጀመሪያ የይገባኛል ጥያቄዎን ካቀረቡበት ጊዜ ጀምሮ ያለው የ52-ሳምንት ጊዜ ነው።
ለምሳሌ፣ በኦክቶበር 2025 ለጥቅማጥቅሞች ካመለከቱ፣ የእርስዎ መደበኛ የመነሻ ዓመት የይገባኛል ጥያቄ ከ2024 ሦስተኛ ሩብ ዓመት እስከ 2025 ሁለተኛ ሩብ ዓመት ድረስ ያለውን ያካትታል። ስለዚህ ይህ የመነሻ ዓመት ከጁላይ 1፣ 2024 ጀምሮ እስከ ጁን 30፣ 2025 ድረስ ይሆናል። የመነሻ ዓመቱ በእያንዳንዱ የቀን መቁጠሪያ ሩብ ዓመት ይለወጣል እና የመጀመሪያውን የይገባኛል ጥያቄዎን በሚያቀርቡበት ሩብ ዓመት ይወሰናል።
-
አማራጭ የመነሻ ዓመት ምንድን ነው?
መደበኛውን የመነሻ ዓመት በመጠቀም ለሥራ አጥነት መድን ብቁ ካልሆኑ፣ በቅርብ ጊዜ የተጠናቀቁትን አራቱን የቀን መቁጠሪያ ሩብ ዓመታት እንጠቀማለን፣ ይህም አማራጭ የመነሻ ዓመት በመባል ይታወቃል።