ማንነትዎን ያረጋግጡ
የኦሬገን የስራ መምሪያ ሰራተኞችን እና የንግድ ድርጅቶችን ለመጠበቅ ማጭበርበርን እና የማንነት ስርቆትን ለመከላከል ጠንክሮ ይሰራል። የስራ አጥነት ጥቅማ ጥቅሞችዎን በፍጥነት ለማግኘት እኛ ማንነትዎን እናረጋግጣለን፡፡ ድርጅቱ ማጭበርበርን እንዴት እንደሚዋጋ እና እራስዎን እና ሌሎችን እራስዎን እና ሌሎችን እንዴት መከላከል እንደሚቻል የበለጠ ማንበብ ይችላሉ።
ማንነትዎን በአቅራቢያዎ የሚገኝ የዩኤስ ፖስታ አገልግሎት ፖስታ ቤት ማረጋገጥ ይችላሉ።
ማንነትዎን ያረጋግጡ
የስራ አጥነት መድን ማጭበርበርን ሪፖርት ያድርጉ
ስለ ስራ አጥነት መድን ማጭበርበር መረጃ ካለዎት፣ እባክዎ ከታች ባለው ማስፈንጠሪያ የማጭበርበር ሪፈራላችንን ይሙሉ ወይም በ 503-947-1995 ወይም 1-877-668-3204 ይደውሉ። የቱንም ያህል መረጃ ቢያቀርቡም፣ የተቀበልናቸውን ሁሉንም ጥቆማዎች እንገመግማቸዋለን። የስራ አጥነት መድን ማጭበርበርን ሲዘግቡ ሊሰጡ የሚችሏቸው ተጨማሪ ዝርዝሮች፣ የበለጠ እንድንመረምር ይረዱናል።
የማጭበርበር ሪፈራል ቅጽ
የፍርድ ውሳኔ
ለስራ አጥነት መድን ጥያቄዎን ከላኩልን በኋላ፣ ብቁ መሆንዎን ለመወሰን እንገመግመዋለን። አንዳንድ ጊዜ፣ ለእርስዎ ጥቂት ተከታታይ ጥያቄዎች ብቻ ሊኖረን ይችላል፣ እና በሌላ ጊዜ ደግሞ የይገባኛል ጥያቄዎ ውስብስብ ሊሆን ወይም ጥልቅ ግምገማ እንድናደርግ የሚጠይቁ ጉዳዮች ሊኖሩት ይችላል።
ይህ ገጽ የእርስዎን የይገባኛል ጥያቄ በጥልቀት እንድንመረምር ወይም ጥቅማጥቅሞችን እንድንከለክል ወይም እንድንቀንስ ሊያደርጉን ስለሚችሉ ሁኔታዎች እንዲሁም እኛ በምንወስነው አስተዳደራዊ ውሳኔ ይግባኝ ለማለት ስላሎት አማራጮች የበለጠ መረጃ ይሰጣል።
ስለ የፍርድ ውሳኔ ሂደት
ሥራ በመፈለግ ላይ እገዛን ያግኙ
ሥራ ለመፈለግ ወይም ለሌላ ኢንዱስትሪ እንደገና ለማሰልጠን፣ በእርስዎ አካባቢ ያሉ የWorkSource Oregon አገልግሎቶች እገዛን ይጠቀሙ፡፡ አብዛኛዎቹ ሰዎች ለጥቅማጥቅሞች ለማመልከት የመጀመሪያ ጥያቄ ካቀረቡ በኋላ ለሥራ ስምሪት አገልግሎቶች እንዲመዝገቡ ይጠበቅባቸዋል፡፡ በኦሬጎን ወይም በኦሬጎን አቅራቢያ የምኖሩ ከሆነ ግን በመደበኛነት በኦሬጎን ውስጥ ለመስራት የምጓዙ ከሆነ በ iMatchSkills መመዝገብ አለብዎት እና የእንደገና ቅጥር ሥራ መመሪያን ለማጠናቀቅ ከ WorkSource Oregon ሠራተኛ ጋር አንድ ላንድ (በኦንላይን ወይም በአካል) ይሥሩ።
ሥራ በመፈለግ ላይ እገዛን ያግኙ
ከሌሎች አጋዥ መርጃዎች ጋር ይገናኙ
የኦሬገን የሥራ መምሪያ እና ሌሎች ድርጅቶች ለሠራተኞች፣ ቀጣሪዎች እና ሌሎች የኦሬገን ነዋሪዎች የተለያዩ ነገሮችን ያቀርባሉ ፡፡
ግብዓቶች
አሰሪዎች
መረጃ እየፈለጉ ያሉ ቀጣሪ ወይም የንግድ ድርጅት ባለቤት ነዎት? ከሥራ ላለማባረር የሚረዱዎትን መረጃ ለማግኘት ስለ ሪፖርት ማቅረቢያ መስፈርቶች፣ አስተዋጽዖዎች እና እንደ Work Share የመሳሰሉት ፕሮግራሞች ለተለየ መረጃ የሥራ ሥምርት መምሪያን የአሰሪ ድረ ገጽ ይጎብኙ፡፡
አሰሪዎች