መዝገበ ቃላት

AAA

  • መስራት የሚችል፦ በአእምሮ እና በአካል መስራት ይችላሉ ማለት ነው።
  • ሥራን በትጋት መፈለግ በሳምንት ቢያንስ አምስት የሥራ ፍለጋ ድርጊቶችን ማጠናቀቅ አለብዎት እና ቢያንስ ከአምስቱ የሥራ ፍለጋ ድርጊቶች መካከል በሁለቱ ከአሠሪዎች ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት መደረግ አለባቸው። ሥራ እየፈለጉ እንደሆነ የሚያሳዩ የድርጊቶች ምሳሌዎች የሥራ ማስታወቂያዎችን መመልከት ፣ የሥራ ፍለጋ መሣሪያዎችን በኦንላይን ላይ መጠቀም ፣ በሙያ ትርኢት ላይ መገኘት ወይም የቃለ መጠይቅ ችሎታዎን የበለጠ ለማሳደግ ስልጠናን መውሰድ ያካትታሉ።
  • ለሥራ መገኘት ሥራ እንዳይቀበሉ የሚከለክሉዎት ገደቦች ሳይኖሩ ለመስራት ፈቃደኛና እና ዝግጁ ነዎት (ለምሳሌ የመጓጓዥያ ጉዳዮች ፣ ህመም ፣ የእረፍት ጊዜያት ወይም የሕፃናት መንከባከቢያ እጥረት) ።

የፍርድ ውሳኔ

ይህ አንድ ግለሰብ ለጥቅማጥቅሞች ብቁ መሆኑን ለማረጋገጥ በተወሰኑ ጉዳዮች ላይ የሚያስፈልገው የስራ አጥነት መድን የይገባኛል ጥያቄ ተጨማሪ የግምገማ ሂደት ነው። የኦሪገን የስራ አጥነት መምሪያ ስለ አንድ ግለሰብ ብቁነት ጥርጣሬ ከፈጠረበት ጥቅማጥቅሞችን ለማግኘት ብቁ መሆኑን ለመመርመር በህግ ይገደዳል። በርካታ ጉዳዮችን በፈጣን ተከታይ ጥያቄዎች መፍታት ይቻላል፣ ይሁን እንጂ ሌሎች ጉዳዮች በፍርድ ሂደት የበለጠ ጥልቅ ግምገማ ያስፈልጋቸዋል። ስለ አስተዳደራዊ ውሳኔዎች እና ፍርድ ውሳኔዎች የበለጠ ይወቁ።

የመሠረት ዓመት

ለሥራ አጥነት መድን ጥቅማ ጥቅሞች የመጀመሪያ የይገባኛል ጥያቄ ከማቅረቡ በፊት የመሠረት ዓመትዎ ካለፉት አምስት የተጠናቀቁ የቀን መቁጠሪያ ሩብ ዓመታት ውስጥ የመጀመሪያዎቹ አራት ናቸው።

የጥቅማጥቅም ዓመት

የጥቅማጥቅም አመትዎ ለስራ አጥነት መድን ጥቅማጥቅሞች የመጀመሪያ ጥያቄዎን ባቀረቡበት የመጀመሪያ ሳምንት የሚጀምር ሆኖ የ52-ሳምንት ጊዜ ነው። ምንም እንኳን የጥቅማጥቅም አመትዎ የ52 ሳምንታት ጊዜ ያለው ቢሆንም፣ አጠቃላይ ጥቅማጥቅሞችን እስከ 26 ጊዜ የሚደርስ የሳምንታዊ ጥቅማጥቅም መጠን ብቻ ሊያገኙ እንደሚችሉና እስከ 52 ሳምንት ጥቅማጥቅምዎ አመት እስከሚያበቃ ድረስ ምንም እንኳን ሁሉንም ጥቅማጥቅሞችዎን የተቀበሉ ቢሆንም አዲስ የኦሪገን የስራ አጥነት መድን ጥያቄ ማቅረብ እንደማይችሉ ልብ ይበሉ።

የተራዘሙ ጥቅማጥቅሞች፣ ከፍተኛ የተራዘሙ ጥቅማጥቅሞች

የተራዘሙ ጥቅማጥቅሞች (EB, በእንግሊዝኛ ምህፃረ ቃል ነው) እና ከፍተኛ የተራዘሙ ጥቅማጥቅሞች (HEB, በእንግሊዝኛ ምህፃረ ቃል ነው) ፕሮግራሞች አንድ ስቴት ከፍተኛ የስራ አጥነት ደረጃ ላይ ባለበት ጊዜ መደበኛ የስራ አጥነት መድን ጥቅማ ጥቅሞችን ያራዝማሉ። ስቴቱ የተራዘሙ ጥቅማጥቅሞች ይኖረው እንደሆነ ለመወሰን አማካይ የስራ አጥነት መጠን በፌዴራል ደረጃ በሶስት ወር ጊዜ ውስጥ ይገመገማል። አማካይ የስራ አጥነት ንፅፅር 8% ወይም ከዚያ በላይ ሲሆን ኦሪገን በHEB ጊዜ ውስጥ ነው እናም እስከ 20 ተጨማሪ ሳምንታት ጥቅማጥቅሞች ይቀርባሉ። መጠኑ ከ 8% በታች ከሆነ ግን ከ 6.5% በላይ ከሆነ ኦሪገን በEB ጊዜ ውስጥ ነው፣ ይህም ደግሞ እስከ 13 ሳምንታት ተጨማሪ ጥቅማጥቅሞችን ይሰጣል።

የተዘጋ የይገባኛል ጥያቄ

$0 ቀሪ ሁሳብ ላይ ሲደርሱ የስራ አጥነት መድን ጥያቄዎ አልቋል እና ከዚያ በኋላ የጥቅማጥቅም ፕሮግራም ምንም ተጨማሪ ገንዘብ አይገኝም።

ጊዜው ያለፈበት የይገባኛል ጥያቄ

መደበኛ የስራ አጥ መድን የይገባኛል ጥያቄ ከ52 ሳምንታት በኋላ ያበቃል። ያ ማለት ምንም እንኳን በመለያዎ ውስጥ ቀሪ ሒሳብ ቢኖርም የይገባኛል ጥያቄዎ ጊዜው ካለፈበት በኋላ ተጨማሪ ሳምንታት ጥቅማጥቅሞችን መጠየቅ አይችሉም ማለት ነው። አዲስ የመጀመሪያ የይገባኛል ጥያቄ ማስገባት ያስፈልግዎታል። ስለ ጊዜው ያለፈባቸው የይገባኛል ጥያቄዎች እና መቼ አዲስ የይገባኛል ጥያቄ እንደሚያስገቡ የበለጠ ይወቁ።

Frances Online

Frances Online የመጀመሪያ ማመልከቻዎን ለbenefits ለማስገባት እና ያቀረቡትን Claim ለመፈተሽ ምርጡ መንገድ ነው። ይህ ስርዓት አድራሻዎን እንዲያዘምኑ፣ direct deposit ገንዘብ እንዲመዘገቡ እና ሌሎችንም ይፈቅድልዎታል። Frances Online በስፓኒሽ እና በእንግሊዝኛ ይገኛል።

ማጭበርበር

የስራ አጥነት መድን ማጭበርበር የሚከሰተው አንድ ሰው የተሳሳተ መረጃ ሲያቀርብ ወይም ጥቅማ ጥቅሞችን ለማግኘት ሆን ብሎ እውነታዎችን ሲደብቅ ነው። ሆን ብለው የተሳሳተ መረጃ ከደበቁ ወይም ሪፖርት ካደረጉ ያ ማጭበርበር ነው። ማጭበርበር ወንጀል ነው እናም የወንጀል ክስን ጨምሮ ቅጣቶችን ሊያስከትል ይችላል። ስለ ስራ አጥነት መድን ማጭበርበር፣ እንዲሁም ስለ ስራ አጥነት የማንነት ስርቆት የበለጠ ይወቁ።

ጠቅላላ ገቢዎች

ግብር እና ተቀናሾች ከመወሰዳቸው በፊት ለስራ የሚያገኙት የገንዘብ መጠን። ጠቅላላ ገቢ ከተጣራ ገቢ ከፍ ያለ መሆን አለበት ።

የማንነት ስርቆት

ሰዎች በህገ-ወጥ መንገድ በኦንላይን የውሂብ ጥሰት የገዙትን ወይም የሰረቁትን ስም እና የግል መረጃ በመጠቀም ወይም የግል መረጃዎን በአጋጣሚ ወይም ሆን ብለው ለሌሎች ሲያጋሩ ለስራ አጥነት ጥቅማጥቅሞች ሊጠይቁ ይችላሉ። አንድ ግለሰብ የስራ አጥነት ጥያቄ ለማቅረብ የሌላ ሰውን መረጃ ሲጠቀም ይህ ድርጊት የማንነት ስርቆት አይነት ነው። የኦሪጎን ነዋሪዎች ስለ ጥቅማጥቅሞች ማመልከቻ ከኦሪገን የቅጥር መምሪያ ወይም ከአሰሪያቸው ማስታወቂያ ሲያገኙ ስለ ማጭበርበር ያውቃሉ። ይህ በእርስዎ ላይ ከተከሰተ፣ የማህበራዊ ዋስትና ቁጥርዎን እና የልደት ቀንዎን ጨምሮ የሆነ ሰው የእርስዎን የግል መረጃ አላግባብ እየተጠቀመበት ነው ማለት ነው። የስራ አጥነት ማንነት ስርቆትን በተቻለ ፍጥነት ያሳውቁን። ስለ የሥራ አጥነት ማንነት ስርቆት እና ስለ ስራ አጥነት መድን ማጭበርበር የበለጠ ይወቁ።

የማንነት ማረጋገጫ

ከስራ አጥነት መድን ፕሮግራም ጥቅማ ጥቅሞችን ለማግኘት ማንነትዎን ማረጋገጥ አለቦት። በእርስዎ የይገባኛል ጥያቄ ጊዜ በተለያዩ ነጥቦች ላይ የማንነት ማረጋገጫ ልንፈልግ እንችላለን። እርስዎ ብቻ የእርስዎን መረጃ እና ጥቅማጥቅሞች ማግኘት እንደሚችሉ ለማረጋገጥ የእርስዎን ማንነት ለማረጋገጥ ብዙ መንገዶች አሉን። ማጭበርበርን በመከላከል የእርስዎን መረጃ እና ጥቅማጥቅሞችን ለመጠበቅ ብዙ መሳሪያዎችን እንጠቀማለን።

በእኛ ማንነትዎን ያረጋግጡ እና እራስዎን ከመጭበርበር ይጠብቁ ገፆች ላይ የበለጠ ይወቁ።

iMatchSkills

ይህ የኦሪገን የቅጥር መምሪያ የኦንላይን ስራ-አገናኝ መሣሪያ ነው። ሊስማማ የሚችለል ስራ ለማግኘት የእርስዎን ክህሎቶች እና የስራ ታሪክ ይጠቀማል። ተጨማሪ ዝርዝሮችን ባቀረቡ ቁጥር፣ iMatchSkills በተሻለ ሊረዳዎ ይችላል። imatchskills.org ላይ ይመዝገቡ።

የመነሻ ወይም የመጀመሪያ ማመልካቻ

የጥቅም ማመልከቻ የጥቅም ዓመት ይመሰርታል። ጥቅሞችን ለማግኘት ብቁ መሆንዎን ለማወቅ፣ ማመልከቻ መሙላት ያስፈልግዎታል። ይህ የመነሻ ማመልከቻ ማቅረብ ይባላል። በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ ነው የመነሻ ጥቅም ማመልከቻ የሚያስገቡት።

የተጣራ ገቢ (የተጣሩ ገቢዎች)

ቀረጦችና ቅንስናሾች ከተወስዱበት በኋላ እርስዎ ወደ ቤትዎ ይዘው የሚገቡት ገቢ።

OED

የኦሪገን የቅጥር መምሪያ (OED, በእንግሊዝኛ ምህፃረ ቃል ነው) የስቴት የስራ ግብረሃይል ኤጀንሲ ነው። የተለያየ፣ ዘርፈ ብዙ-ክህሎት ያለው የሰው ኃይል በማዳበር ለኦሪጋውያን የሥራ ስምሪት እናስተዋውቃለን፣ እና በስራ አጥነት ጊዜ ድጋፍ እንሰጣለን። ስለእኛ የበለጠ ይወቁ

የአንላይን የይገባኛል ጥያቄ ስርዓት/Online Claim System (OCS)

Frances Online የኦንላይን የይገባኛል ጥያቄ ስርዓት ምትክ ነው።

ከመጠን በላይ የተከፈለ ክፍያ

ከመጠን በላይ ክፍያ የሚፈፀመው፣ የሚከሰተው እርስዎ ብቁ ያልሆኑበት ክፍያ ሲከፍልዎት ነው። አንዳንድ ከመጠን በላይ ክፍያዎች የሚከሰቱት ሰዎች ትክክለኛ ወይም ከፊል መረጃ ሲሰጡን ነው። የድርጅቱ ስህተቶችም ከመጠን በላይ ክፍያዎችን ያስከትላሉ። ሌሎች ደግሞ አዲስ መረጃ ከተቀበልን በኋላ በይግባኝ ላይ ያደረግነው ውሳኔ ሲቀየር ሊከሰቱ ይችላሉ ።

ከመጠን በላይ ክፍያዎች ሲኖሩ እነርሱን ለማስመለስ የመሞከር ህጋዊ ግዴታ አለብን ። እርስዎ የማይከፍሉት ከሆነ ፣ እርስዎ ብቁ ከሆኑባቸው ከማናቸውም የወደፊት ጥቅሞች የዕዳውን መጠን በመቀነስ ያንን ዕዳ በተለምዶ “እናካክሳለን” ።

ምክንያታዊ ማረጋገጫ

ለአስተማሪዎች ፣ ከእረፍት በኋላ እንደምትመለሱ “ምክንያታዊ ማረጋገጫ” ካልተሰጣችሁ በትምህርት ቤት የእረፍት ጊዜ ወቅት ጥቅሞችን ለማግኘት ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ ። በአጠቃላይ ምክንያታዊ ማረጋገጫ ማለት በተመሳሳይ ወይም በተመሳሳይ አቅም በተመሳሳይ የደመወዝ መጠን (ወይም በ 90% ውስጥ) ሥራ ተሰጥቶዎታል ማለት ነው። ስራ ማግኘቱ በጽሑፍ ፣ በቃል ወይም በተዘዋዋሪ ሊሆን ይችላል ። ሆኖም ፣ በዚያ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ማመልከቻዎን መገምገም አለብን።

ስለ ስራ አጥነት መድን እና የትምህርት ቤት ሰራተኞች የበለጠ ያንብቡ።

በራስ ተቀጣሪ

ከአሰሪ ይልቅ ለራስህ የምትሰራ ከሆነ ራስህ ተቀጣጥረሃል።

ስለ ሥራ አጥነት ኢንሹራንስ የሚሰጥ ሥልጠና (TUI)

ይህ ፕሮግራም ብቁ የሆኑ ተፈናቃዮች ትምህርት ቤት ሄደው እንዲማሩ እና ቤተሰቦቻቸውን መንከባከባቸውን እንዲቀጥሉ እና ሥራ እንዲያገኙ በተመሳሳይ ጊዜ መደበኛ ጥቅሞችን እንዲያገኙ ያስችላቸዋል። ፕሮግራሙ በራሱ ለስልጠና ክፍያ አይደለም፣ ነገር ግን በምትኩ ትምህርት ቤት የሙሉ ጊዜ ላይ ሳል ሳምንታዊ ማመልከቻን ከሥራ ፍለጋ መስፈርቶች ያስወግዳል፡፡

 ስለ ስራ አጥነት መድን ፕሮግራም የበለጠ ይወቁ

ስራ አጥ

በአጠቃላይ፣ በማንኛውም ሳምንት ከ40 ሰዓት በታች በሰሩበት እና ከሳምንታዊ የጥቅማጥቅም መጠን ያነሰ ባገኙበት ስራ እንደ ፈቱ ተደርገው ይቆጠራሉ።

የስራ አጥነት መድን/Unemployment insurance (UI, በእንግሊዝኛ ምህፃረ ቃል ነው)

የስራ አጥነት መድን/Unemployment insurance (UI) ጥቅማጥቅሞች ሥራ አጥ ሲሆኑ ያጡትን ገቢ በከፊል ይተካሉ። ይህ የህዝብ እርዳታ አይደለም። አሰሪዎች የUI ፕሮግራምን ይደግፋሉ፣ እናም የUI ግብሮች ከሰራተኛ ክፍያ ቼኮች አይያዙም።

U.S. Bank ReliaCard®

የቅጥር መምሪያው በU.S. Bank ReliaCard ቪዛ ዴቢት ካርድ ወይም በቀጥታ በማስያዝ በኤሌክትሮኒክ መንገድጥቅማጥቅሞችን ይከፍላል። ለቀጥታ ተቀማጭ ገንዘብ ካላመለከቱ፣ ReliaCard የሚላክልዎት ይሆናል።

የጥበቃ ሳምንት

የጥበቃ ሳምንት ሳምንታዊ ማመልከቻ የሚያቀርቡበት እና ሁሉንም የብቁነት መስፈርቶችን የሚያሟሉበት የመጀመሪያው ሳምንት ነው። ጥቅሞችን መቀበል ከመጀመርዎ በፊት የኦሬገን ሕግ በአንድ ማመልከቻ አንድ የጥበቃ ሳምንት ይፈልጋል ። የጥበቃ ሳምንት በመሆኑ ለርሱ ክሬዲት ወይም ዋጋ ለመቀበል ለሳምንቱ ማመልከቻ ማስገባት ያስፈልጋል።

ሳምንታዊ የጥቅማጥቅም መጠን (WBA, በእንግሊዝኛ ምህፃረ ቃል ነው)

የእርስዎ ሳምንታዊ የጥቅማጥቅም መጠን (WBA) ከጠቅላላ የመነሻ ዓመት ጠቅላላ ገቢዎ 1.25% የሚያህል ነው። በኦሪገን ህግ መሰረት፣ ከዝቅተኛው የጥቅማጥቅም መጠን ያነሰ ወይም ሊቀበሉት ከሚችሉት ከፍተኛ የጥቅማጥቅም መጠን በላይ አይሆንም።

። ለምሳሌ፣ በሰዓት 20 ዶላር የሚያገኝ ሰራተኛ፣ ላለፈው አመት በሳምንት 40 ሰአታት የሰራ ሰራተኛ በሳምንት 520 ዶላር ጥቅማጥቅሞችን ያገኛል። $20 x 40 = $800 በሳምንት x 52 ሳምንታት = 41,600 ዶላር። $41,600 x 1.25% = $520.

ዝቅተኛው እና ከፍተኛው መጠን በየዓመቱ ይቀየራል። ከጁላይ 1፣ 2024:

  • ዝቅተኛ ሳምንታዊ የጥቅሙ መጠን: $196
  • ከፍተኛ ሳምንታዊ የጥቅሙ መጠን: $836

ሳምንታዊ የይገባኛል ጥያቄ

የስራ አጥነት ጥቅማጥቅሞችን ለማግኘት በየሳምንቱ የይገባኛል ጥያቄ ማቅረብ አለብዎት። ይህ ከመጀመሪያው የይገባኛል ጥያቄ የተለየ ነው። ሳምንታዊ የይገባኛል ጥያቄ ባለፈው ሳምንት የምንልክልዎን ገንዘብ መጠን ይወስናል። ሳምንታዊ የይገባኛል ጥያቄዎች ላለፈው ሳምንት ቀርበዋል እናም በእሁድ ይጀምሩ እና በቅዳሜ ይጠናቀቃሉ። በቅዳሜ ለተጠናቀቀው ሳምንት ሳምንታዊ የይገባኛል ጥያቄዎን ለማቅረብ እስከ እሁድ ድረስ መጠበቅ አለብዎት።

የስራ መጋራት/ Work Share

የስራ መጋራት/Work Share ፕሮግራም ቀጣሪዎች የስራ ግብረ-ኃይላቸውን ለማሰናበት ሌላ አማራጭ ይሰጣል። አሰሪዎች የስራ ሰዓታቸውን በመቀነስ የተካኑ ሰራተኞችን በአስቸጋሪ ጊዜ ማቆየት ይችላሉ። ሰዓታቸው የተቀነሰባቸው ብቁ የሆኑ ሰራተኞች የስራ አጥነት መድን የተወሰነ ክፍል የጠፋውን ደመወዝ ለማካካስ ያገኛሉ። ስለ የስራ መጋራት/Work Share ኦሪገን የበለጠ ይወቁ።

WorkSource ኦሪገን

የስራ መጋራት/Work Share ኦሪገን ስራ ፈላጊዎችን በሺዎች ከሚቆጠሩ የስራ እድሎች እና የስልጠና እድሎች ጋር ያገናኛል እናም አሰሪዎችን ብቁ ከሆኑ እጩዎች ጋር ያገናኛል። አገልግሎቶች ነፃ ናቸው። WorkSource ኦሪገን የሚከተሉትን አገልግሎቶች ይሰጣል፦

  • የስራ ሪፈራሎች
  • እንደ ቃለ-መጠይቅ ዝግጅት፣ ሬዚውሜ/ሲቪ መፃፍ እና መሰረታዊ የኮምፒዩተር እውቀትን የሚሸፍኑ አውደ ጥናቶች
  • የሙያ ስራ እቅድ ማውጣት
  • በስኮላርሺፕ እገዛ የትምህርት እና የስልጠና እድሎች

1099-G

1099-G ጥቅሞች ላገኙ ሰዎች የሚላክ የግብር ቅጽ ነው። የፌዴራል እና የእስቴት የገቢ ግብሮችን ለአገር ውስጥ ገቢ አገልግሎት (አይአርኤስ) እና ለኦሬገን የገቢ መምሪያ ሲያቀርቡ ይጠቀሙበታል ። የእርስዎን በFrances Online ውስጥ ማውረድ ይችላሉ።