አጋሮች

አጋሮቻችን እና ማህበረሰብ አቀፍ ድርጅቶችን እኛን ስለረዱን እናመሰግናለን። በሁሉም የOregon ሠራተኞች ውስጥ ያለውን የሥራ አጥነት መድህን ግንዛቤን ለማሳደግ፣ በመላው Oregon አጋሮች ያስፈልጉናል። ጥቅማጥቅሞችን ለማግኘት እና ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ለማሻሻል አላማ ለስራ አጥነት መድህን ለመግባት ብቁ የሆኑ ሰራተኞችን ቁጥር ለመጨመር እየሰራን ነው።

ተልዕኳችንን ለማሳካት የሚረዱን ተጨማሪ አጋሮችን እንፈልጋለን። ማህበረሰብን መሰረት ያደረጉ ድርጅቶች ውጤታማ የመረጃ እና የድጋፍ ምንጮች እንደሆኑ እናውቃለን፣ ምክንያቱም እርስዎ በማህበረሰብዎ ተዓማኒነት ስላለዎት። ድርጅትዎ ሰራተኞች የሚገባቸውን ጥቅሞች እንዲያገኙ በሚከተለው መንገድ ሊረዳቸው ይችላል፡

  • ግንዛቤን በማሻሻል
  • እንዴት ማመልከት እንደሚቻል በማጋራት
  • የብቁነት መስፈርቶች ላይ ያለን ግንዛቤ በማሳደግ

እኛን ለመቀላቀል፣ እባክዎን ወደ navigator@employ.oregon.gov ኢሜይል ያድርጉ።

የሥራ አጥ መድህን ፕሮግራም የአጋሮች መመሪያ

በእኛ የሥራ አጥ መድህን ፕሮግራም የአጋሮች መመሪያ ውስጥ ሠራተኞችን ስለመርዳት የበለጠ ይወቁ።

የማህበራዊ ሚድያ አጠቃቀም መመሪያ

የOregon Employment Department በ TwitterInstagramFacebook፣ እና LinkedIn ላይ በንቃት ይሳተፋል። እባክዎ ይዘታችንን ለማህበረሰብዎ ያጋሩ።

የማህበራዊ ሚድያ አጠቃቀም መመሪያ

መልዕክት ለማስተላለው የሚያስችሉ የሚታተሙ ቁሳቁሶች

ስለ ሥራ አጥነት ጥቅማጥቅሞች እና የይገባኛል ጥያቄ እንዴት እንደሚገባ ለማህበረሰቡ ለማሳወቅ እነዚህን የሚታተሙ መልዕክት ማስተላለፊያዎች ይጠቀሙ።

የጽሑፎች መመሪያ ስብስብ