የይግባኝ ሂደት

ጥቅማጥቅሞችን በምንቀንስበት ወይም በምንከለክልበት በማንኛውም ጊዜ የአስተዳደር ውሳኔን የሚገልጽ ደብዳቤ እንልክልዎታለን። በተሰጠው የአስተዳደር ውሳኔ ጋር የማይስማሙ ከሆነ፣ ጉዳይዎን በፍርድ ቤት እንዲታይ ከአስተዳደራዊ ችሎቶች ቢሮ ችሎት የመጠየቅ እንዲሁም ውሳኔው እንደገና በይግባኝ መንገድ እንዲታይ የመጠየቅ መብት አልዎት። በአንዳንድ ሁኔታዎች አሰሪዎ ተመሳሳይ መብት አለው።

በፍርድ ቤት ችሎት ጊዜ፣ ከአስተዳደራዊ ችሎቶች ቢሮ የአስተዳደር ህግ ዳኛ በጉዳዩ ላይ የተሳተፉ ሰዎችን ምስክር በመስማት ውሳኔ ይሰጣል። የፍርድ ቤት ቀጠሮ ችሎቶች ብዙውን ጊዜ የሚከናወኑት በስልክ ነው።

በአስተዳደር የተሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ይግባኝ ከጠየቁ፣ በየሳምንቱ ጥቅማጥቅሞችን ለመቀበል መመዝገብዎን ይቀጥሉ። የይግባኙ ውሳኔ የእርስዎን ጉዳይ የሚደግፍ ከሆነ፣ በጊዜው ለጠየቁት ሳምንታት ብቻ ነው የሚከፈሉት።

ጊዜው የጠበቀ ይግባኝ ያስገቡ

በአስተዳደር የሚሰጡ ውሳኔዎች በፖስታ ከተላኩ ከ20 ቀናት በኋላ ይጸናሉ፤ ስለዚህ ጉዳይዎ በፍርድ ቤት ችሎት እንዲታይ ከፈለጉ በፍጥነት የይግባኝ ጥያቄ ያስገቡ። በጊዜው ይግባኝ ካላቀረቡ ዋናው አስተዳደራዊ ውሳኔ እንደገና እንዲታይ አይደረግም።

የፍርድ ቤት ችሎት ይጠይቁ

በአስተዳደር ውሳኔዎ ውስጥ የተካተተው ቅጽ የይግባኝ ጥያቄ እንዴት ማቅረብ እንደሚቻል የሚገልጽ መመሪያ ይኖረዋል። እንዲሁም በሚከተሉት መንገዶች ይግባኝ ማቅረብ እና ችሎት መጠየቅ ይችላሉ።

  • ጥያቄው በፋክስ ቁጥር 503-947-1335 በመላክ።
  • ጥያቄው ወደ Unemployment Insurance – Hearings, 875 Union St NE, Salem, OR 97301 በመላክ
  • በስ.ቁ 503-947-3149 በመደወል እና ሁሉንም አስፈላጊ መረጃዎች የያዘ መልእክት በመተው።

ሁሉንም አስፈላጊ መረጃዎች ማካተትዎን ለማረጋገጥ Request for a Hearing (ቅጽ 2602) መሙላት ይችላሉ። በሚያቀርቡት ጥያቄዎ ውስጥ የሚከተለውን መረጃ ያካትቱ፦

  • የማህበራዊ ደህንነት ቁጥርዎን[Social Security Number(SSN)] ወይም የደንበኛ መለያ ቁጥርዎን [Customer Identification Number (CID)]።
  • የአስተዳደር ውሳኔ ቁጥር። ይህ ቁጥር በፖስታ በላክንልዎ ደብዳቤ ላይ ይገኛል።
  • ይግባኝ የሚሉበት ውሳኔ የተሰጠበት ቀን።
  • በውሳኔው ለምን እንደማይስማሙ ለመረዳት የሚረዳን መረጃ።
  • በፍርድ ቤቱ ችሎት ለመገኘት የማይችሉበት የተወሰኑ ቀናት ወይም ሰዓቶች።

የቋንቋ እርዳታ እና ሌሎች አስፈላጊ ድጋፎችን ያለምንም ወጪ እናቀርብልዎታለን።

የፍርድ ቤት ችሎቶች እና የይግባኝ አሰራር ሂደት በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ በአስተዳደራዊ ችሎቶች ቢሮ ድረገጽ ድህረ ገጽ ላይ ማግኘት ይችላሉ።

አድራሻዎ ትክክል መሆኑን ያረጋግጡ

የፍርድ ቤት ችሎት ከጠየቁ እና አድራሻዎን ማስተካከል ከፈለጉ፡ ለአስተዳደራዊ ችሎቶች ቢሮ በስ.ቁ 503-947-1515 እንዲሁም ለስራ አጥነት ኢንሹራንስ ማዕከል ማሳወቅ አለብዎት።