የስልጠና የስራ አጥነት መድን/Training Unemployment Insurance
የስልጠና የስራ አጥነት መድን (TUI) መርሃ ግብር የተፈናቀሉ — ስራ አጥ የሆኑ እና ወደ ቀድሞው ኢንዱስትሪያቸው የመመለስ — አዳዲስ ክህሎቶችን እያገኙ ራሳቸውን እና ቤተሰባቸውን የመደገፍ ዕድል የሌላቸውን ሰራተኞች ይረዳል። ከዚያም ወደ ስራ ግብረ ኃይል ተመልሰው ስራቸውን ማሳደግ ይችላሉ።
በTUI መርሃግብር ስር የተፈናቀሉ ሰራተኞች ከስራ አጥነት መድን መርሃ ግብር ጥቅማጥቅሞችን እያገኙ እያለ ስልጠና ሊያገኙ ወይም ትምህርት ቤት ሊከታተሉ ይችላሉ። የ TUI መርሃ ግብር ስልጠና አይሰጥም ወይም ለስልጠና ክፍያ አይከፍልም፤ ይሁን እንጂ ጥቅማጥቅሞችን ለማግኘት መፈለግ እና ለስራ ዝግጁ የመሆንን መስፈርት ያስወግዳል። በዚህም መንገድ፣ በሙሉ ጊዜ ትምህርት መከታተል ይችላሉ።
በዚህ ገጽ ላይ:
- ስለ TUI ፕሮግራም መታወቅ ያለባቸው በጣም አስፈላጊ ነገሮች ምንድን ናቸው?
- ለTUI መርሃግብር ብቁ የሆነው ማነው?
- የ TUI መርሃግብር ጥቅማጥቅሞች ምንድ ናቸው?
- በ TUI መርሃግብር ውስጥ ሳለሁ ምን አይነት ስልጠና ማግኘት እችላለሁ?
- በ TUI መርሃግብር ውስጥ ሳለሁ ሌሎች ምን ጥቅማጥቅሞችን ማግኘት እችላለሁ?
- በ TUI መርሃግብር ውስጥ እንዴት መሳተፍ እችላለሁ?
- በ TUI መርሃግብር ውስጥ እንዴት ንቁ ሆኜ መቆየት እችላለሁ?
- ስለ ስራ ፍለጋ መስፈርቶችስ?
- የስልጠና ወይም የትምህርት ቤት ወጪስ?
- ትምህርት ቤቱ ምን ማድረግ ይኖርበታል?
- ጥያቄዎች አሉዎት?
ስለ TUI ፕሮግራም መታወቅ ያለባቸው በጣም አስፈላጊ ነገሮች ምንድን ናቸው?
በየዓመቱ፣ የTUI መርሃግብር በመቶዎች የሚቆጠሩ ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ሰራተኞች ወደ የስራ ግብረ ሃይል መመለስ ይችሉ ዘንድ ትምህርት እንዲከታተሉና የተፈቀደ ስልጠና እንዲከታተሉ ያግዛቸዋል። ሆኖም ግን መርሃግብሩ የተወሰኑ መስፈርቶች አሉት።
- የ TUI መርሃግብር ለትምህርት ወይም ለስልጠና መክፈል አይችልም፣ ሆኖም ግን በስልጠና ላይ ላሉ ሰዎች ጥቅማጥቅሞችን ይሰጣል።
- የተፈናቀሉ ሰራተኞች ብቻ ናቸው ብቁ የሚሆኑት። ያመለከቱ እንደሆነ፣ የተፈናቀሉ ሰራተኛ መሆንዎን ለማወቅ ጥያቄዎችን እንጠይቅዎታለን።
- የሚማሩበት ትምህርት ቤት ወይም ስልጠና ፈቃድ ወይም እውቅና ሊኖረው ይገባል።
- ትምህርት ቤቱ ወይም ስልጠናው የሙሉ ጊዜ መሆን መቻል አለበት።
ትምህርት ቤቱ ወይም የስልጠና ተቋሙ እርስዎ የላኩልንን ማመልከቻ ገጽ 3 ላይ መሙላት አለባቸው።
ለTUI መርሃግብር ብቁ የሆነው ማነው?
ከስራ የተፈናቀለ ሰራተኛ ማለት ወደ ቀድሞው ኢንደስትሪ ወይም ስራ የመመለስ እድል እንደሌለው የቅጥር መምሪያ የገለፀው ማንኛውም ግለሰብ ነው። ይህም ወታደራዊ ዘማቾችን ያካትታል።
በኢኮኖሚ ድቀት ወይም በኩባንያው መዘጋት ምክንያት የተፈናቀሉ ሰራተኛ ሊሆኑ ይችላሉ። ለምሳሌ ያህል በቴክኖሎጂ እድገት የተነሳ በተዘጋው ፋብሪካ ውስጥ የገጠማ መስመር ሰራተኛ ከሆኑ፣ ወደዚያ ስራ የመመለስ ዕድልዎ ከፍተኛ ነው።
ለተከታታይ ስምንት ሳምንታት ስራ አጥ የነበሩ ሰዎችም ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ።
ብቁ መሆንዎን እርግጠኛ ካልሆኑ፣ እባክዎ ማመልከቻውን ይሙሉ እና መስፈርቶቹን የሚያሟሉ እንደሆነ ለመለየት ልንረዳዎት እንችላለን።
የ TUI መርሃግብር ጥቅማጥቅሞች ምንድ ናቸው?
በTUI መርሃግብር፣ ከስራ አጥነት መድን መርሃግብር የተፈናቀሉ ሰራተኞች ሙሉ ጊዜያቸውን ትምህርታቸውን መከታተል ይችላሉ። ስራ ለመፈለግ ምንም መስፈርት የለም። ተሳታፊዎች እስከ 26 ሳምንታት የሚደርሱ ጥቅማጥቅሞችን ከማንኛውም የፌዴራል ወይም የስቴት ማራዘሚያዎች ሊያገኙ ይችላሉ።
አንዳንድ የTUI ተሳታፊዎች ለተፈናቀሉ ሰራተኞች ተጨማሪ ስራ አጥነት (SUD) መርሃግብር ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ፣ ይህ ማራዘሚያ ለTUI መርሃግብር ብቻ ይገኛል።
በ TUI መርሃግብር ውስጥ ሳለሁ ምን አይነት ስልጠና ማግኘት እችላለሁ?
እውቅና ካለው የኮሚኒቲ ኮሌጅ፣ ዩኒቨርሲቲ ወይም የሙያ ፕሮግራም የሙሉ ጊዜ ስልጠናን ማግኘት ይችላሉ። መርሃግብሩ በዩኤስ የትምህርት መምሪያ ዕውቅና ሊሰጠው የሚገባ ሲሆን፣ በኦሪገን እውቅና ያለው ፈቃድ መስጠት ወይም በክልላዊ የሰው ኃይል ኢንቨስትመንት ቦርድ መታወቅ ይኖርበታል።
በአጠቃላይ፣ ስልጠናው የሙሉ ጊዜ መሆን አለበት። ሙሉ ጊዜ የሚለው ትርጓሜው በስልጠናው ተቋሙ ወይም በትምህርት ቤቱ ላይ የተመሰረተ ነው። አስፈላጊ ክፍሎች ከሌሉ ወይም እርስዎ ስልጠና ለመጨረስ የተወሰኑ ክፍሎች ብቻ ከፈለጉ ልዩ ሁኔታዎችን ልናስቀምጥ እንችላለን።
አንድ መርሃግብር መስፈርቶቹን እንደሚያሟላ እርግጠኛ ካልሆኑ፣ እባክዎ ያመልክቱ።
በ TUI መርሃግብር ውስጥ ሳለሁ ሌሎች ምን ጥቅማጥቅሞችን ማግኘት እችላለሁ?
የTUI ተሳታፊዎች ለተፈናቀሉ ሰራተኞች ተጨማሪ ስራ አጥነት ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ። እነዚያም ጥቅማጥቅሞች ለተጨማሪ 26 ሳምንታት ወይም የተፈቀደልዎ ስልጠና እስኪያበቃ ድረስ፣ ከሁለቱ አንዱ መጀመሪያ ለተከሰተው ሊገኙ ይችላሉ።
በ TUI መርሃግብር ውስጥ እንዴት መሳተፍ እችላለሁ?
ለ TUI መርሃግብር ከማመልከትዎ በፊት ከስራ አጥነት መድን መርሃግብር ጥቅማጥቅሞች ለማግኘት የመጀመሪያ ማመልከቻ ማስገባት አለብዎት። ከዚያ በኋላ የTUI መርሃግብር ማመልከቻውን ወደ የኦሪገን የቅጥር መምሪያ መላክ አለብዎት። የተፈናቀሉ ሰራተኛ መሆንዎን ለማወቅ እንድንችል፣ ማመልከቻዎን እንገመግመዋለን እና ጥያቄዎችን እንጠይቅዎታለን። ብቁ መሆንዎን እርግጠኛ ካልሆኑ፣ እባክዎን ያመልክቱና እኛ እንረዳዎታለን።
ማመልከቻዎን ካጸደቅን፣ በTUI መርሃግብር ላይ ለመሳተፍ የእውቅና ማረጋገጫ ይደርስዎታል።
እንደ መደበኛ የይገባኛል ጥያቄ አቅራቢ ከስራ አጥነት መድን መርሃግብር ተመሳሳይ መጠን ያገኛሉ። ለተፈናቀሉ ሰራተኞች ተጨማሪ የስራ አጥነት (SUD) ጨምሮ ለማናቸውም የስቴት ወይም የፌደራል ማራዘሚያዎች ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ።
በ TUI መርሃግብር ውስጥ እንዴት ንቁ ሆኜ መቆየት እችላለሁ?
በ TUI መርሃግብር ውስጥ በሚሳተፉበት ጊዜ ጥቅማጥቅሞችን መቀበልዎን ለመቀጠል፣ የሚከተሉትን ማድረግ አለብዎት፦
- በየሳምንቱ የተፈቀደውን ስልጠና ይከታተሉ።
- እያንዳንዱ ሳምንት ካለቀ በኋላ ሳምንታዊ የይገባኛል ጥያቄዎን ያስገቡ።
- በእያንዳንዱ የትምህርት ዘመን መጨረሻ ላይ በስልጠናው ላይ አጥጋቢ ተሳትፎን የሚያሳይ የውጤት ሰርተፍኬት ወይም የማጠናቀቂያ ሰርተፍኬት ወይም ሌላ ሪፖርት ለኦሪገን የቅጥር መምሪያ ያቅርቡ።
ስለ ስራ ፍለጋ መስፈርቶችስ?
ለ TUI መርሃግብር ፈቃድ እስኪያገኙ እና የሙሉ ጊዜ ስልጠና ላይ እስከሚገኙ ድረስ የስራ ፍለጋ መስፈርቶች ይቀራሉ። ለ TUI መርሃግብር የOED ፍቃድ እስኪያገኙ ድረስ በጠየቁት እያንዳንዱ ሳምንት መስራት፣ ለስራ መገኘት እና በንቃት ስራ መፈለግ መቻል አለብዎት።
ፈቃድ ካገኙ እና የሙሉ ጊዜ ስልጠናውን ከጀመሩ በኋላ ስራ መፈለግ አይጠበቅብዎትም። በተፈቀደው ስልጠና ውስጥ ሙሉ ጊዜ ተመዝግበው እስካሉ እና በጥቅማጥቅሞችዎ ላይ ሂሳብ እስካለዎ ድረስ ይህ ነፃ መሆን ይቀጥላል። ሁሉንም ጥቅማጥቅሞችዎን ከጠየቁ በኋላ ለ TUI መርሃግብር ብቁ አይሆኑም።
የስልጠና ወይም የትምህርት ቤት ወጪስ?
ለስልጠናዎ ወይም ለትምህርትዎ ወጪ ሃላፊነት የሚሆነው የእርስዎ ነው። የTUI መርሃግብር ለስልጠናዎ ስልጠና ወይም የገንዘብ ድጋፍ አይሰጥም። መርሃግብሩ በትምህርት ቤት ወይም በስልጠና ወቅት ስራ መፈለግን ብቻ ያስወግዳል።
ትምህርት ቤቱ ምን ማድረግ ይኖርበታል?
የስልጠና ተቋሙ ወይም የት/ቤቱ ተወካይ ለTUI መርሃግብር የማመልከቻዎን ገጽ 3 መሙላት አለበት።
ጥያቄዎች አሉዎት?
ስለ የገንዘብ ድጋፍ ወይም የስልጠና አማራጮች ጥያቄዎች ካሉዎት፣ የአካባቢዎን የስልጠና አቅራቢ ወይም የአካባቢዎን WorkSource Oregon ያነጋግሩ። የአካባቢዎን የስልጠና አቅራቢ በ CareerOneStop ወይም WorkSource Oregon ማግኘት ይችላሉ።
እንዴት ማመልከት እንዳለብዎት ጨምሮ ስለ TUI መርሃግብር ጥያቄዎች ካሉዎት ወደ ልዩ መርሃግብሮች ማዕከል በ 503-947-1800 ወይም 800-436-6191 ይደውሉ። የTUI ተወካይ መርሃግብሩን በዝርዝር ያብራራል እና ማመልከት የፈለጉ እንደሆነ ማመልከቻ ይሰጥዎታል።
ማመልከቻ