የስራ አጥነት መድን ጥቅማጥቅሞችን ለመቀበል ማንነትዎን ያረጋግጡ

በአካል ቀርበው ማንነትዎን ማረጋገጥ የሥራ አጥነት ኢንሹራንስ ጥቅማጥቅሞችን ለመቀበል የሚያስፈልግ እርምጃ ነው። ይህም የማንነት ማጭበርበርን ለመከላከል ይረዳል።

ተቀባይነት ያላቸውን የማንነት ማረጋገጫ ሰነዶች በአካል ማቅረብ ያስፈልግዎታል። ይህ ከFrances Online ጋር የተያያዙ የማንነት ማረጋገጫ ደብዳቤዎች በተጨማሪ ነው።

ማንነትዎን ለማረጋገጥ ሰነዶችን ለማቅረብ ሁለት አማራጮች አሉዎት፦

  • በፕሮግራሙ የሚሳተፉ የUSPS ፖስታ ቤቶች
  • የWorkSource Oregon ቦታ

ማንነትዎን የት ለማረጋገጥ እንደሚመርጡ ጥቅማጥቅሞችን ለመቀበል ብቁነትዎን አይጎዳም።

መዘግየትን ለማስወገድ ማንነትዎን በወቅቱ ያረጋግጡ

ለጥቅማጥቅሞች የመጀመሪያ ማመልከቻዎን ካጠናቀቁ በኋላ፣ በተለምዶ በጥቂት ቀናት ውስጥ ደብዳቤ እንልክልዎታለን። ደብዳቤው ማንነትዎን በአካል ለማረጋገጥ የመጨረሻ ቀን እና ይህን መስፈርት እንዴት ማሟላት እንደሚችሉ የሚገልጹ መመሪያዎችን ይይዛል። ደብዳቤውን ከላክንበት ቀን በኋላ 10 የሥራ ቀናት ይኖሩዎታል።

የዳግም ሥራ ቅጥር አገልግሎቶች ብቁነት ግምገማ፣ ወይም RESEA፣ እንዲያጠናቅቁ ልንጠይቅዎት እንችላለን። ማንነትዎን በሚያረጋግጡበት ተመሳሳይ ጊዜ ይህንን በWorkSource Oregon ማድረግ ይችላሉ። የሁለቱም ተግባራት የመጨረሻ ቀን ተመሳሳይ ይሆናል።

ደብዳቤው በFrances Online መለያዎ ውስጥም ይታያል። ፖስታዎን እና Frances Onlineን በየጊዜው ያረጋግጡ።

የመጨረሻ ቀኑን ካለፉ

ማንነትዎን እስከ መጨረሻ ቀኑ ድረስ ካላረጋገጡ፣ ጥቅማጥቅሞችን ለመቀበል ብቁ አይሆኑም። ዳግም ብቁ ለመሆን ይህን መስፈርት ማሟላት አለብዎት።

የመጨረሻ ቀኑን ካለፉ፣ በተቻለ ፍጥነት የማንነት ማረጋገጫውን ያጠናቅቁ። የመጨረሻ ቀኑን ቢያልፉም ሂደቱ አይለወጥም። እንዲሁም ለደንበኛ አገልግሎት መደወል አያስፈልግዎትም። ከዚህ በታች ያሉትን መመሪያዎች በመጠቀም በተቻለ ፍጥነት ማንነትዎን ያረጋግጡ።

የUSPS ፖስታ ቤት

ማንነትዎን በአቅራቢያዎ የሚገኝ የዩኤስ ፖስታ አገልግሎት ፖስታ ቤት ማረጋገጥ ይችላሉ።  የዳግም ሥራ ቅጥር አገልግሎቶች ብቁነት ግምገማዎች ሊጠናቀቁ የሚችሉት በWorkSource Oregon ብቻ ነው። 

ማንነትዎን በፖስታ ቤት ማረጋገጥ እንዲችሉ Frances Online (ፍራንሲስ ኦንላይን) ላይ መመዝገብ አለብዎት።

  • Frances Online ላይ ሎጊን ያድርጉ
  • "I Want To..." (“... እፈልጋለሁ”) የሚለውን ይምረጡ
  • “Verify My Identity” (ማንነቴን ማረጋገጥ) ከሚለው መደብ ውስጥ “Verify My Identity In-Person at a Post Office” (ማንነቴን በአካል በፖስታ ቤት ውስጥ ማረጋገጥ) የሚለውን ይምረጡ።
  • መመሪያዎቹን ይከተሉ

ከተመዘገቡ በኋላ በUSPS ፖስታ ቤት ውስጥ በአካል ለማረጋገጥ ሰባት ቀናት ይኖርዎታል።  ይህንን በጊዜ ካላጠናቀቁ፣ በFrances Online ላይ በ“Verify My Identity In-Person at a Post Office” መስፈንጠሪያ በኩል በድጋሚ መመዝገብ ይችላሉ። 

USPS እነዚህን የመታወቂያ ዓይነቶች ይቀበላል፦

  • በስቴት የተሰጠ መንጃ ፈቃድ
  • በስቴት የተሰጠ መታወቂያ ካርድ
  • የዩኤስ ጦር ኃይሎች ወይም የባለመለዮ አገልግሎቶች መታወቂያ ካርድ (የአድራሻ ማስረጃ ያስፈልጋል)
  • የዩኤስ ፓስፖርት (የአድራሻ ማስረጃ ያስፈልጋል)

USPS በድረገጹ ላይ ተቀባይነት ስላላቸው የመታወቂያ ዓይነቶች የበለጠ መረጃ አለው።  የምዝገባ ሂደቱ በአቅራቢያዎ ያሉ ማንነትዎን ማረጋገጥ የሚችሉባቸው የUSPS ፖስታ ቤቶችን ዝርዝር ይናገራል።

የUSPS ሠራተኞች ስለ ሥራ አጥነት ኢንሹራንስ ማንኛውንም ጥያቄ መመለስ አይችሉም። 

በUSPS ፖስታ ቤት ውስጥ አገልግሎቶች ከእንግሊዝኛ ውጪ በሌላ ቋንቋ ላይገኙ ይችላሉ። 

St. Johns Bridge rises above and Willamette River at twilight in Portland.

WorkSource Oregon

ለጥቅማጥቅሞች ካመለከቱ በኋላ፣ አብዛኛዎቹ ደንበኞች ከWorkSource Oregon ወኪል ጋር እንዲገናኙ ይጠየቃሉ። ወኪሉ ሥራ ለማግኘት እና የሙያ ግቦችን ለማሳካት እቅድ እንዲያዘጋጁ ይረዳዎታል። ይህ ስብሰባ የዳግም ሥራ ቅጥር አገልግሎቶች ብቁነት ግምገማ ወይም RESEA ይባላል። የአንድ-ለ-አንድ ክፍለ ጊዜዎ እስከ 90 ደቂቃ ሊወስድ ይችላል እና በአካል ወይም በቨርቹዋል ወይም ምናብ ስብሰባ ሊካሄድ ይችላል።

በመግቢያ መረጃ ስብሰባዎ ወቅት ማንነትዎን በአካል ለማረጋገጥ መምረጥ ይችላሉ። ሁለቱንም መስፈርቶች ለማጠናቀቅ የመጨረሻ ቀኑ ተመሳሳይ ነው። ሁለቱንም ተግባራት በWorkSource Oregon በአንድ ጊዜ ማጠናቀቅ በጣም የተለመደው ምርጫ ነው።

በአቅራቢያዎ ያለ የWorkSource Oregon ማዕከል ለማግኘት የWorkSource Oregon ድረ ገጽን ይጠቀሙ። በአካል ወይም በመስመር ላይ ስብሰባ ቀጠሮ ለማስያዝ ይደውሉ። WorkSource Oregon በግዛቱ አቀፍ ያሉ የገጠር አካባቢዎችን የሚያገለግሉ በርካታ ተንቀሳቃሽ ማዕከላትን ያስተዳድራል

እባክዎ ከዚህ በታች ያሉትን ተቀባይነት ያላቸው የማንነት ማረጋገጫ ሰነዶች ይመልከቱ እና በWorkSource Oregon ለሚኖርዎት ስብሰባ ይዘዋቸው ይምጡ።

ጠቃሚ ምክሮች፦

  • የRESEA ስብሰባ እንዲኖርዎት የማይጠየቁ ቢሆንም፣ አሁንም በWorkSource Oregon ማዕከል ማንነትዎን ማረጋገጥ ይችላሉ።
  • ከእንግሊዝኛ ውጭ በሌላ ቋንቋ እርዳታ ከፈለጉ፣ በWorkSource Oregon ማንነትዎን ማረጋገጥ ይችላሉ። በ833-685-0845 ወደ WorkSource Oregon የቋንቋ ተደራሽነት መስመር ይደውሉ።
  • WorkSource Oregon ለአካል ጉዳተኞች ነፃ እርዳታ ይሰጣል።

ጥያቄዎች አሉዎት?

ማንነትዎን በማረጋገጥ ላይ ተጨማሪ እገዛ የሚፈልጉ ከሆነ፣ እኛን ማነጋገር የሚቻሉባቸው መንገዶች ገጽ ላይ እርዳታ ለመጠየቅ በርካታ አማራጮች አሉ።

እኛን ማነጋገር የሚቻሉባቸው መንገዶች