ግብዓቶች እና ተደራሽነት
የኦሪገን የቅጥር መምሪያ እና ሌሎች ድርጅቶች ለሰራተኞች፣ ለአሰሪዎች እና ለሌሎች የኦሪገን ነዋሪዎች የተለያዩ መገልገያዎችን ይሰጣሉ። ለተጨማሪ ዝርዝሮች፣ ከዚህ በታች ያሉትን ርዕሶች እና ማስፈንጠሪያዎች ይመልከቱ።
በዚህ ገጽ ላይ:
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ይህ መረጃ አስፈላጊ ነው። የኦሬጎን የቅጥር መምሪያ (The Oregon Employment Department, OED) የእኩል እድል ኤጀንሲ ነው። አገልግሎቶቻችንን መጠቀም እንዲችሉ OED ነፃ እገዛን ይሰጣል። አንዳንድ ምሳሌዎች የምልክት ቋንቋ እና የንግግር ቋንቋ አስተርጓሚዎች፣ በሌሎች ቋንቋዎች የተጻፉ ጽሑፎች፣ ትልቅ ህትመት፣ ኦዲዮ እና ሌሎች ቅርጸቶች ናቸው። እገዛ ለማግኘት፣ እባክዎ ወደ unemployment.oregon.gov/am ይሂዱ እና ያግኙን ቅጽ የሚለውን ጠቅ ያድርጉ ወይም በ 877-345-3484 ይደውሉልን። የTTY ተጠቃሚዎች 711 ይደውላሉ።
ስለ ቋንቋ የመዳረሻ መመሪያችን እና የቋንቋ መዳረሻ ሂደታችን የበለጠ ማንበብ ይችላሉ።
ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች
ከስራ አጥነት መድን ጋር ያልተገናኘ፣ እንደ የሚከፈልበት የቤተሰብና የህክምና ፈቃድ፣ የጤና መድን ሽፋን ወይም በማህበረሰብዎ ውስጥ ግብዓቶች ያሉ ሌሎች የጥቅማ ጥቅሞችን ለማግኘት ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ።
የሚከፈልበት እረፍት ኦሪገን
የሚከፈልበት ፈቃድ ኦሪገን ግለሰቦች ለቤተሰቦቻችን እና ለጤንነታችን እና ደህንነታችን ላይ ተጽእኖ ለሚፈጥሩ ለብዙ የህይወት ወሳኝ ወቅቶች የሚከፈልበት እረፍት እንዲወስዱ የሚያስችላቸው አዲስ ፕሮግራም ነው። ስለ ጥቅማ ጥቅሞች እና ማን ብቁ እንደሆነ በ paidleave.oregon.gov ላይ መረጃ ይገኛል።
WorkSource ኦሪገን
WorkSource ኦሪገን የንግድ ድርጅቶችን እና ሰራተኞችን ለስኬታማነት ከሚያስፈልጋቸው ግብዓቶች ጋር በማገናኘት የስራ እድገትን ለማነቃቃት አብረው የሚሰሩ የህዝብና የግል አጋሮች አውታረመረብ ነው። ስለ አገልግሎቶች እና ቦታዎች በ worksourceoregon.org ላይ መረጃ ይገኛል።
የጤና መድን ሽፋን
የጤና መድን ሽፋን ከጠፋብዎ ወይም የጤና መድን ሽፋን ከሌለዎት ለነጻ ወይም ዝቅተኛ ወጭ የጤና እቅድ ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ። healthcare.oregon.gov ን ይጎብኙ ወይም በ 1-855-268-3767 ይደውሉ።
ሌሎች ግብዓቶች
211Info በኦሪገን ውስጥ ወይም በአካባቢዎ ማህበረሰብ ውስጥ የሚገኙ ሌሎች ግብዓቶችን እንዲያገኙ ሊረዳዎት ይችላል፣ ለምሳሌ፦
- የቤት ኪራይ ለመክፈል ወይም መኖሪያ ቤት ለማግኘት ማገዝ
- የፍጆታ ሂሳቦችን ለመክፈል ማገዝ
- ግሮሰሪ ወይም ሌላ ምግብ ለማግኘት ማገዝ
- የልጅ እንክብካቤ ለማግኘት እና ለመክፈል ማገዝ
- የገንዘብ ጥቅማ ጥቅሞች
- ለቤት ውስጥ ጥሰት ሁኔታዎች አስቸኳይ እገዛ
- በመጓጓዣ እርዳታ
- ለስደተኛ እና ሰነድ ለሌላቸው ማህበረሰቦች ድጋፍ
- ሌሎች የማህበረሰብ ግብዓቶች
የበለጠ ለማወቅ እና ግብዓቶችን ለማግኘት 211info.org ን ይጎብኙ። እንዲሁም የሚከተሉትን ማድረግ ይችላሉ፦
- በ 2-1-1 ወይም 1-866-698-6155 ይደውሉ (የጻ የቋንቋ አስተርጓሚዎች ይገኛሉ)
- TTY 711 ይደውሉ እና 1-866-698-6155 ይደውሉ
- የእርስዎን ዚፕ ኮድ ወደ 898211 (TXT211) (እንግሊዝኛ እና ስፓኒሽ) ፅሁፍ ይላኩ።
ኢሜይል help@211info.org (እንግሊዝኛ እና ስፓኒሽ)