የንግድ ህግ ፕሮግራም

The federal በ 2015 በንግድ ማስተካከያ እርዳታ ድጋሚ ፈቃድ ህግ (የንግድ ሕግ) የተቋቋመው የፌዴራል የንግድ ማስተካከያ እርዳታ (TAA) መርሃ ግብር በውጭ ንግድ ስራቸው ላይ አሉታዊ የሆነ ተጽዕኖ ለደረሰባቸው ብቁ የአሜሪካ ሰራተኞች ጥቅማጥቅሞችን እና አገልግሎቶችን ይሰጣል።

በመላ ሀገሪቱ፣ የገጠርም ሆነ የከተማ ማህበረሰቦች የተገነቡት በተወሰኑ ኢንዱስትሪዎች ዙሪያ ነው። የውጪ ውድድር በእነዚህ ኢንዱስትሪዎች ላይ ተጽዕኖ በሚያሳድርበት ጊዜ ጉዳቱ የሚያርፈው ግለሰቦቹ ብቻ ሳይሆን መላው ማህበረሰቦችም ጭምር ላይ ነው።

በኦሪገን እና በሌሎች ቦታዎች ይህ የፌደራል መርሃ ግብር ኩባንያዎች ወደ ውጭ አገር ከተዘዋወሩ በኋላ የማምረቻ ፋብሪካዎች ሲዘጉ፣ እንደ የውጭ ውድድር ባለ ምክንያት የተነሳ ስራ ያጡ ሰዎችን ይረዳል። መርሃ-ግብሩ ለእነዚህ ከስራ የተሰናበቱ ሰራተኞች አዳዲስ እና የረጅም ጊዜ ስራዎችን ለመምራት የሚያስፈልጉ ክህሎቶችን፣ የትምህርት ማስረጃዎችን፣ ግብዓቶችን እና ድጋፎችን እንዲያገኙ ዕድሎችን ይሰጣል።

በዚህ ገጽ ላይ:

የንግድ ህግን ማጠቃለያ የሚያቀርቡ ቪዲዮዎች በእንግሊዝኛበስፓኒሽበሩሺያኛ፣ እና በቬትናምኛ ይገኛሉ። ሙሉውን የአጫዋች ዝርዝር በዩቲዩብ ይመልከቱ።

የንግድ ህግ መመሪያ መፅሃፍቶች በእንግሊዝኛበስፓኒሽበቬትናምኛ እና በሩሺያኛ ይገኛሉ።

ጥያቄዎች አሉዎት?

የማዕከላዊ ንግድ ህግ ክፍል የስራ ሰዓታት ከ8 ሰዓት እስከ ምሽቱ 5 ሰዓት ነው። የማዕከላዊ የንግድ ህግ ክፍልን በዚህ አድራሻ ማግኘት ይችላሉ፦

ማዕከላዊ የንግድ ህግ ክፍል

የኦሪገን የቅጥር መምሪያ

875 Union St. NE #084

Salem, OR 97311

ስልክ፦ 503-947-3096

ከክፍያ ነፃ፦ 877-639-7700

ፋክስ፦ 503-947-1676

የፋክስ ከክፍያ ነፃ፦ 855-851-0168

ኢሜይል፦ taacentral@employ.oregon.gov

TTY፦ 7-1-1