የሥራ አጥነት የይገባኛል ጥያቄ ውሳኔ

ደሞዝዎን እና ሰአታትዎን በጥንቃቄ ይገምግሙ። መረጃው የተሳሳተ ከሆነ፣ የይገባኛል ጥያቄዎ እንደገና እንዲወሰን መጠየቅ ይችላሉ። የሥራ አጥነት ጥያቄን ውሳኔ የሚገልጽ ደብዳቤ በፖስታ እንልክልዎታለን። መግለጫው የሚከተሉትን ያሳየዎታል፡-

  • ሳምንታዊ የጥቅማጥቅም መጠን እና የሚከፈለው ከፍተኛ ጥቅማጥቅm - እነዚህ ቁጥሮች በሳምንት ውስጥ ሊያገኙ የሚችሉትን ከፍተኛ መጠን እና በአጠቃላይ በይገባኛል ጥያቄዎ ላይ ሊገኝ የሚችለውን መጠን ይወክላሉ::
  • የሰሩላቸው አሰሪዎች፣ እና በጥያቄዎ መነሻ አመት ለእያንዳንዱ ሩብ አመት ያሳወቁዎት ደመወዝ እና ሰዓታት - ስለ ሩብ አመት እና የመነሻ አመታት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ከታች በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎችን ይመልከቱ ።
  • የጥቅማጥቅም አመትዎ የሚጀምርበት እና የሚያበቃበት ቀናት - በዚህ የይገባኛል ጥያቄ ላይ በእነዚህ ቀናት መካከል ለሚቆዩ ሳምንታት ብቻ ጥቅማጥቅሞችን መጠየቅ ይችላሉ።
  • ይህ መግለጫ የመጀመሪያ ውሳኔ ወይም ድጋሚ ውሳኔ ለመሆኑ ።

የኦሬገን የስራ አጥነት ጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ለአንድ አመት ይገኛል፣ ይህም ካመለከቱበት ሳምንት ጀምሮ 52 ሳምንታት ነው። ይህ የ52-ሳምንት ጊዜ የጥቅማጥቅምዎ ዓመት ይባላል። ያ አመት እስኪያልቅ ድረስ ሌላ አዲስ የኦሬገን የይገባኛል ጥያቄ ማቅረብ አይችሉም።

የስራ አጥነት የይገባኛል ጥያቄ ውሳኔ የሚከተለው ከሆነ ይነግርዎታል፡-

  • በመነሻ አመትዎ ከ500 ሰዓታት በታች ስለሰሩ ትክክለኛ የይገባኛል ጥያቄ የለዎትም።
  • ለተለዋጭ ለመነሻ ዓመት የይገባኛል ጥያቄ ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ - ስለ ተለዋጭ መነሻ ዓመታት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ከታች በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎችን ይመልከቱ፡፡
  • ከቀድሞ ቀጣሪዎችዎ ደመወዝ እና ሰዓት እየጠየቅን ነው።
A pedestrian bridge crosses Spring Creek at Collier Memorial State Park near Chiloquin. Evergreen trees stand in the background.

ሩብ ምንድን ነው?

ዓመቱ ሩብ 1 (Q1) ፣ ሩብ 2 (Q2) ፣ ሩብ 3 (Q3) እና ሩብ 4 (Q4) በመባል የሚታወቁት በአራት የባጀት ሩብ ክፍሎች የተከፈለ ነው። የሩብ ርዝማኔዎች እንደሚከተለው ናቸው፡፡

  • ሩብ ዓመት 1፣ ጥር፣ የካቲት እና መጋቢት

ሩብ ዓመት 2፣ ሚያዚያ፣ ግንቦትና ሰኔ

  • ሩብ ዓመት 3፣ ሐምሌ፣ ነሐሴ እና መስከረም

ሩብ ዓመት 4፣ ጥቅምት፣ ህዳር እና ታህሳስ

የመነሻ ዓመት ምንድን ነው?

የመነሻ ዓመትዎ ከ“የጥቅማ ጥቅም ዓመት” በፊት ካለፉት አምስት የተጠናቀቁ የቀን መቁጠሪያ ሩብ ዓመታት የመጀመሪያዎቹ አራት ሲሆን የጥቅማጥቅም ዓመትዎ የመጀመሪያ የይገባኛል ጥያቄዎን ካቀረቡበት ጊዜ ጀምሮ ያለው የ52-ሳምንት ጊዜ ነው።

ለምሳሌ፣ ለጥቅማጥቅሞች በጥቅምት 2022 ካመለከቱ፣ የእርስዎ መደበኛ የመነሻ ዓመት የይገባኛል ጥያቄ ከ2021 እስከ 2022 ሁለተኛ ሩብ ሶስተኛውን ሩብ (ከሀምሌ እስከ መስከረም ያሉትን ሶስት ወራት) ያካትታል። ስለዚህ፣ ይህ መነሻ ዓመት ከሀምሌ 1፣ 2021 እስከ ሰኔ 30፣ 2022 ድረስ ይሆናል። የመነሻ አመት በእያንዳንዱ የቀን መቁጠሪያ ሩብ ጊዜ ይለዋወጣል እና የመጀመሪያ የይገባኛል ጥያቄዎን በሚያስገቡበት ሩብ ይወሰናል፡፡

ተለዋጭ የመነሻ ዓመት ምንድን ነው?

መደበኛውን የመነሻ ዓመት በመጠቀም ለሥራ አጥነት ኢንሹራንስ ብቁ ካልሆኑ፣ አማራጭ የመነሻ ዓመት በመባል የሚታወቀውን አራቱን በጣም በቅርብ ጊዜ የተጠናቀቁትን የቀን መቁጠሪያ ሩብ ክፍሎች እንጠቀማለን።

በዳኝነት ግምገማ ወቅት፣ ውሳኔዎቻችንን አሁን ባለን መረጃ መሰረት እናደርጋለን። ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ ሁኔታዎ ከተቀየረ ምርመራውን እንደገና እንከፍታለን እና ውሳኔያችንን ማቆም ወይም መቀልበስ እንችላለን።